1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያን ባህል በዘጋቢ ፊልም

እሑድ፣ መጋቢት 20 2001

የባህል መድረክ ዝግጅታችን የኢትዮጵያን ባህልና ታሪክ በሲኒማ ጥበብ ለማስተዋወቅና ጠብቆ ለማቆየት እየተንቀሳቀሱ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ይዞ ይቀርባል። ስለኢትዮጵያ የሚያወሱ አራት የተለያዩ ዘጋቢ ፊልሞችንም ይተነትናል።

https://p.dw.com/p/HMJl
ላሊበላ
ላሊበላምስል picture-alliance/ dpa
በበርካታ የምዕራቡ ዓለም የብዙሀን መገናኛ ስለኢትዮጵያ ሲነሳ፤ ከቱባ ባህልና ታሪኳ ይልቅ፤ ረሀብ፣ እርዛትና የነጣ ድህነቷ ቀድሞ ሲከሰት ነው የሚስተዋለው። በአንፃሩ ሁኔታው እያንገበገበ ሰላም ቢያሳጣቸው፤ የሀገራቸውን በጎ ጎን ለማስተዋወቅ፤ የሲኒማ ጥበባቸውን እንደመሳሪያ አንስተው የሚታገሉም አልታጡም። የዋሽንግተኑ ዘጋቢያችን አበበ ፈለቀ፤ አራት ዘጋቢ ፊልሞችን ቃኝቶ የሚከተለውን አጠናቅሯል።