1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያዉን ሠራተኞች እሮሮ በሳዑዲ

ዓርብ፣ ታኅሣሥ 12 2005

በኮንትራት ሠራተኝነት ወደአረብ ሀገሮች የሚሄዱ ኢትዮጵያዉያን የሚደርስባቸዉ በደል ከጊዜ ወደጊዜ መባባሱ ይሰማል። በቅርቡ ስዑዲ አረቢያ ዉስጥ ህይወታቸዉን ያጡና የአካል ጉዳት የደረሰባቸዉ እህቶች ጉዳይ የችግሩን አስከፊነት ያመለክታል።

https://p.dw.com/p/177lp
ምስል Nebiyu Sirak

በኮንትራት ሠራተኝነት ወደአረብ ሀገሮች የሚሄዱ ኢትዮጵያዉያን የሚደርስባቸዉ በደል ከጊዜ ወደጊዜ መባባሱ ይሰማል። ባሳለፍነዉ አንድ ዓመት ብቻ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዉን ከስራ ጋ በተያያዘና በአሰሪዎች በሚደርስባቸዉ ጥቃት ከአካል መጉደል እስከህልፈተ ህይወት ለሚያደርስ ከፍተኛ አደጋ እንደተጋለጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ። የጄዳዉ ወኪላችን ነብዩ ሲራክ የላከልን ዘገባ እንደሚያስረዳዉ ሁለት ኢትዮጵያዉያን የኮንትራት ሰራተኞች በአሰሪያቸዉ ጥቃት እንደተፈጸመባቸዉ ታዋቂ የሳዉዲ ጋዜጦች ሳይቀሩ በዝርዝር ዘግበዉታል። ግለሰቡ በስለት በሰነዘረዉ ጥቃት የአንዲቱን ህይወት ቀጥፏል፤ ሌላዋን ለጉዳት ዳርጓል።

ነብዩ ሲራክ

ሸዋዬ ለገሠ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ