የኢትዮጵያዉያኑ አዲስ መኖርያ - ጅቡቲ

የኢትዮጵያዉያኑ አዲስ መኖርያ - ጅቡቲ

የኢትዮጵያዉያን የህይወት መንገድ

ጅቡቲ ለጉረቤት ሃገር ለኢትዮጵያ በስትራቴጅያዊና በኢኮኖሚያዊ ጥቅም አኳያ ዋንኛ ሃገር ናት። ይህ ደግሞ በተለይ በጎርጎረሳዉያኑ አቆጣጠር በ 1990 ዎቹ ዓመታት ኤርትራ ከኢትዮጵያ ስትገነጠል የባህር ወደብዋን ካጣች በኋላ ነዉ። የባሕር ወደብ የሌላት ኢትዮጵያ ዛሬ ከዉጭ የምትገዛቸዉን ሸቀጦች በሙሉ በጅቡቲ ወደብ በኩል ማስገባት ጀምራለች። የኢትዮጵያ መርከቦች የታጁራን የባህር - ሰላጤ በመቅዘፍ ለኢትዮጵያ እጅግ አሰፈላጊ ሸቀጦችን ለሃገሪቱ ያቀርባሉ።

የኢትዮጵያዉያኑ አዲስ መኖርያ - ጅቡቲ

በባቡር ምትክ ከባድ የጭነት ማመላለሻዎች

በ 20 ኛዉ ምዕተ ዓመት ከአዲስ አበባ ጅቡቲ የተዘረጋዉ የባቡር ሃዲድ ከጅቡቲ ወደ አዲስ አበባ ሸቀጦችን በማመላለስ ጥቅም ይሰጥ እንደነበር ይታወቃል። ከ 21 ኛዉ ክፍለ ዘመን መግብያ ገደማ ጀምሮ ግን ከጅቡቲ በኩል ሸቀጥ የማመላለሱ ተግባር ከቀን ወደ ቀን ትልልቅ የጭነት ማመላለሻዎች እየተቀየረ መጣ። አሁን በቻይናዉያን ኩባንያ እየተገነባ ያለዉ የአዲስ አበባ ጅቡቲ አዲስ የባቡር ሃዲድ በጎርጎርዮሳዊዉ 2016 መባቻ ሥራዉን እንደሚጀምር ተመልክቶአል።

የኢትዮጵያዉያኑ አዲስ መኖርያ - ጅቡቲ

ትንሽዋ ኢትዮጵያ በጅቡቲ

የኢትጵዮጵያ አጉራባች በሆነችዉ በጅቡቲ በርካታ ኢትዮጵያዉያን ይኖራሉ። በጅቡቲ ወደ 50.000 ኢትዮጵያዉያን እንዳሉ ነዉ የሚገመተዉ። አብዛኞቹ ደግሞ በደርግ ዘመነ መንግሥት ሃገር ጥለዉ ተሰደዉ የመጡ መሆናቸዉን አቶ አሸናፊ ሃራጌ የኢትዮጵያዉያን አሰባሳቢ ማዕከልን በመወከል ይናገራሉ። እንደ አቶ አሸናፊ ጅቡቲ ለኢትዮጵያዉያን የሥራ ሃገር ናት። በጎርጎረሳዉያኑ 1991 ዓ,ም የተገረሰሰዉ የሶሻሊስት ርዕዮተ ዓለምን አራማጁ የደርግ መንግሥት በመቶ ሺህ የሚቆጠር ህዝብን በግፍ አሰቃይቶአል፤ ገድሎአል።

የኢትዮጵያዉያኑ አዲስ መኖርያ - ጅቡቲ

እንደ ሃገራችን እንመገባለን

የኢትዮጵያዉያን ማኅበረሰብ በሚሰባሰቡበት ማዕከል፤ ባህላዊ ምግብና መጠጥ ይገኛል። «ወደ ጅቡቲ የመጣሁት የሚገኘዉ ገንዘብ የተሻለ በመሆኑ ነዉ» ይላሉ በስተቀኝ በኩል የሚታዩት በአንድ የጭነት ማመላለሻ ድርጅት ዉስጥ የሚያገለግሉት አቶ ኃይሌ ገብረ መድህን።

የኢትዮጵያዉያኑ አዲስ መኖርያ - ጅቡቲ

ሥራ ፍለጋ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቋንቋ አማርኛ በጅቡቲ ኦቦክ እና ታጁራ አካባቢዎች በስፋት ይነገራል። ጅቡቲ የሚኖሩት ኢትዮጵያዉያን በሙሉ ወደ ጅቡቲ የመጡበት ምክንያት አንድ ነዉ፤ «ሥራ ፍለጋ»። በጅቡቲ አንድ የፅዳት ሠራተኛ፤ በአዲስ አበባ አንድ ፕሮፊሰር የሚያገኘዉን የደሞዝ መጠን ያገኛል፤ ሲል በታጁራ የሚኖረዉ ሁሴን ይገልፃል። ግን ይላል ሁሴን ኢትዮጵያ ያለዉ ምቹዉ የአየር ፀባይ ይናፍቀኛል። እዚህ እጅግ ሞቃታማ ነዉ።

የኢትዮጵያዉያኑ አዲስ መኖርያ - ጅቡቲ

የየዕለት ትግል

በየግዜዉ የሚገኘዉን እንደ ፅዳት ሥራ የመሳሰሉትን ስራዎች እሰራለሁ። «እዚህ የሙሉ ቀን ሥራ የማግኘት ዕድል እጅግ ከባድ ነዉ» ሲል ከአስራ ሁለት ዓመት በፊት ወደ ጅቡቲ የመጣዉ የ 24 ዓመቱ ሳሙኤል ይናገራል። ሳሙኤል ያለምንም መታወቅያ የጅቡቲን ድንበር ሲያቋርጥ በመገኘቱ አራት ወራት በጅቡቲ እስር ቤት ቆይቶአል። « ያለ ፓስፖርት ወደ የትም መንቀሳቀስ አልችልም፤ እንደ እቃ መርከብ ላይ ካለታጨኩ በስተቀር ይላል፤ ሳሙኤል።

የኢትዮጵያዉያኑ አዲስ መኖርያ - ጅቡቲ

እንደ ሸቀጥ ታሽጎ ስለመጓጓዝ ታሪክ

የ25 ዓመቱ አሌክስና የ 29 ዓመቱ ዘሪሁን ጅቡቲ ዉስጥ ያለምንም መታወቅያ ነዉ የሚኖሩት። እቃ አመላላሽ መርከብ ላይ በመንጠልጠል ከኬፕታዉን እንስከ ሲንጋፖር ሄደዋል። አሁን ግን መኪና በማጠብ እንዲሁም ከቆሻሻ ላይ ዉዳቂ በመሰብሰብ ነዉ የዕለት ኑሮአቸዉን የሚገፉት። « እዚህ ከፖሊስ እየተሸሸግን እንደ ዉሻ ነዉ የምንኖረዉ» ሲል ዘሪሁን ይናገራል፤ አሌክስ በበኩሉ «አይደለም ልክ እንደ ወታደር ነዉ ኑሮአችን» ባይ ነዉ።

የኢትዮጵያዉያኑ አዲስ መኖርያ - ጅቡቲ

ሐይማኖት

በጅቡቲ አብዛኛዉ ነዋሪ ሙስሊም ነዉ። ዘወትር እሁድ ኢትዮጵያዉያን ኦርቶዶክስ ክርስትያኖች በኢትዮጵያዉያን መሰብሰብያ ማዕከል አጠገብ በሚገኘዉ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ-ክርስትያን ለፀሎት ይሰበሰባሉ። «በሌሎች ሃገሮች ይህን ሐይማኖት ማራመድ ተቀባይነት አይኖረዉ ይሆናል፤ እዚህ ግን ህዝቡ ምንም አያጤነዉም» ሲል ገብረመድህን ይገልጻል።

የኢትዮጵያዉያኑ አዲስ መኖርያ - ጅቡቲ

የኦርቶዶክስ ክርስትና ሐይማኖት ተከታዮች በጅቡቲ

ሴቶች ወደ ቤተ-ክርስትያን ሲመጡ ነጠላቸዉን ተከናንበዉ ነዉ። በቤተ-ክርስትያኑ እጣን ጭስ ይታያል፤ ሴቶች የቅድስት ማርያም ምስልን ይሳለማሉ። ቄሶችም ወደ ምዕመናኑ እየተጠጉ መስቀላቸዉን ያሳልማሉ።

የኢትዮጵያዉያኑ አዲስ መኖርያ - ጅቡቲ

መቆየት ወይስ ወደ ሃገር መመለስ?

በጅቡቲ የሚኖሩ በርካታ ኢትዮጵያዉያን ወደ ሃገር መመለስ ወይስ እዚህ መቅረት የሚለዉን ሃሳብ በአዕምሮአቸዉ ያመላልሳሉ። በተለይ ደግሞ ህጻናት ልጆች ያልዋቸዉ ኢትዮጵያዉያን ዉሳኔ ላይ መድረስ ተስኖአቸዋል።

ምስራቅ አፍሪቃዊትዋ ሃገር የኢትዮጵያና ትንሽዋ አጎራባች ሃገር ጅቡቲ ጥሩ የሆነዉን ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት በማሻሻል ላይ ይገኛሉ። በአሁኑ ወቅት ወደ 50,000 ኢትዮጵያዉያን በተራራማዋ ሃገር በጅቡቲ ይኖራሉ፤ አብዛኞቹ ወደ ጅቡቲ የሚመጡት ደግሞ ሥራ ፍለጋ ነዉ።

ተከታተሉን