1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያዉያን መገደልና የሐገሪቱ ምክር ቤት

ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 13 2007

የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሊቢያና ደቡብ አፍሪቃ ዉስጥ ሰሞኑን በግፍ የተገደሉ ኢትዮጵያዉያንን ለማሰብ የሠወስት ቀን ብሕራዊ ሐዘን አወጀ።ምክር ቤቱ ዛሬ ባደረገዉ ሥብሰባዉ በሁለቱም ሥፍራዎች የተፈፀሙትን ግድያዎች አጥብቆ አዉግዟል።

https://p.dw.com/p/1FC2k
Das Parlamentsgebäude in Äthiopiens Hauptstadt Addis Abeba
ምስል DW

የምክር ቤቱ እንደራሴዎች በየተራ ባሰሙት ንግግር «አይ ኤስ» የተሰኘዉ አሸባሪ ድርጅት የገደላቸዉንም ሆነ ደቡብ አፍሪቃ ዉስጥ የተገደሉትን ኢትዮጵያዉያን ቤተሰቦችን መንግሥት ሊያፅናናቸዉና ሊደግፋቸዉ ይገባል። ምክር ቤቱ ዛሬ ባሰለፈዉ ዉሳኔ መሠረት ከነገ-ጀምሮ ባንዲሮች በግማሽ ሠንደቅ ይዉለበለባሉ።

ጌታቸዉ ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

ነጋሽ መሀመድ

ሂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ