1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች የተቃዉሞ ሠልፍ

ዓርብ፣ ሐምሌ 19 2005

የተቃዉሞ ሠልፉና የሥብሰባዉ አስተባባሪዎች እንደገለፁት ዩናይትድ ስቴትስ፥ ካናዳ፥ አዉስትሬሊያ በተለያዩ የአዉሮጳና የመካካለኛዉ ምሥራቅ ከተሞች አደባባይ የወጣዉ ኢትዮጵያዊ ሙስሊም የኢትዮጵያ መንግሥት ሐማኖታዊ ነፃነትን እና ሠብአዊ መብትን እንዲያከብር፥ ጠይቋል

https://p.dw.com/p/19Eta
Muslime feiern das Ende des Ramadans im Nationalstadium von Addis Abeba, Äthiopien Copyright: Getachew Tedla/DW, 19.08.2012, Addis Abeba, Äthiopien
ምስል DW/Tedla Getachew

በመላዉ ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች ዛሬ በተለያዩ ከተሞች ባደረጉት የአደባባይ ሠልፍና ስብሰባ በሐይማኖታዊ ጉዳያችን ጣልቃ ገባ ያሉትን የኢትዮጵያ መንግሥትን አወገዙ። የተቃዉሞ ሠልፉና የሥብሰባዉ አስተባባሪዎች እንደገለፁት ዩናይትድ ስቴትስ፥ ካናዳ፥ አዉስትሬሊያ በተለያዩ የአዉሮጳና የመካካለኛዉ ምሥራቅ ከተሞች አደባባይ የወጣዉ ኢትዮጵያዊ ሙስሊም የኢትዮጵያ መንግሥት ሐማኖታዊ ነፃነትን እና ሠብአዊ መብትን እንዲያከብር፥ ጠይቋል።የሙስሊም መሪዎችን ማሰሩን እና የእምነት ተቋማትና ትምሕርት ቤቶችን ወርሷል በማለትም አዉግዘዋል። የየሐገራቱ መንግሥታትም በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ተፅዕኖ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።እዚያዉ ኢትዮጵያ ዉስጥ በየሳምንቱ አርብ በየመስጊዱ የሚደረገዉ ተቃዉሞ ዛሬም እንደቀጠለ ነዉ።ዩናይትድ ስቴትሱን የተቃዉሞ ሠልፍ በተመለከተ የዋሽግተን ዲሲ ወኪላችን አበበ ፈለቀን በስልክ አነጋግሬዋለሁ።

ነጋሽ መሐመድ

አበበ ፈለቀ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ