1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያዉያን ሴቶች ሚና በሐገሪቱ ኤኮኖሚ

እሑድ፣ ጥቅምት 9 2007

በግሉ መስክም የየራሳቸዉን ድርጅቶችና ተቋማት የመሠረቱ የሚመሩና የሚያስተዳደሩ ሴቶች ቁጥር እያደገ ነዉ።የእድገቱ ደረጃ፤ እድገቱን ለማገዝ የሚያስፈልገዉ ድጋፍና ፖሊሲ፤ ፖሊሲዉን ገቢር ለማድረግ ያለዉ ፍላጎት ግን አሁንም አነጋጋሪ ነዉ።

https://p.dw.com/p/1DXuG
ምስል picture alliance / landov

ለዛሬዉ ዉይይታችን የኢትዮጵያዉያን ሴቶች ሚና በሐገሪቱ ኤኮኖሚ የሚል ጥቅል ርዕስ ሰጥተነዋል።እንደምናቀዉ ሴቶች ከቤት እመቤትነት ባለፈ በሁሉም መስኮች፤ በሁሉም ዓለም ያላቸዉ ተሳትፎ ከወንዶቹ ጋር ሲነፃፀር አንስተኛ ነዉ።

ኢትዮጵያን በመሳሰሉ አዳጊ ሐገራት ደግሞ ሴቶች የሚሳተፉባቸዉ መስኮችም፤ የሚሳተፉት ሴቶች ቁጥርም ሲበዛ ዉስን ነዉ።ከቅርብ ዓመታት ወዲሕ ሥልጣን የያዙ መንግሥታት ለራሳቸዉ ፖለቲካ ጥቅምም ሆነ ፍላጎት ወይም በመብት ተሟጋች ተቋማት፤ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትን በመሳሰሉ ዓለም አቀፍ ማሕበራት ግፊትና ድጋፍ የሴቶችን ተሳፎ ለማሳዳግ እየጣሩ አንዳዶቹም ተጨባጭ ለዉጦች እያሳዩ ነዉ።

በርካታ ሴቶችን የመንግሥት ሥልጣን በተለይ ደግሞ የምክር ቤት እንደራሴነት ሥልጣን እንዲይዙ በማድረግ ከአፍሪቃ ሩዋንዳ ቀዳሚዉን ሥፍራ ይዛለች።ላይቤሪያ እና ማላዊ በምርጫም ሆነ በዉርስ ሴት ፖለተከኞች ለፕሬዝዳትነት በቅተዉባቸዋል።የአፍሪቃ ሕብረትም በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ በሴት ዲፕሎማት እየተመራ ነዉ።

Karte Äthiopien englisch

ኢትዮጵያ ዉስጥም ሴቶች ለወትሮዉ ከሚታወቀዉ ከአስተማሪነት፤ከፀሐፊነት፤ ከነርስ፤ ከእደ-ጥበብ ባለሙያነት ወጣ ባሉ ሙያዎች የሚቀጠሩ፤ በፖለቲካዉ እና በማሕበራት እንቅስቃሴዎች የሚሳተፉ ሴቶች ቁጥር ጨምሯል።በግሉ መስክም የየራሳቸዉን ድርጅቶችና ተቋማት የመሠረቱ የሚመሩና የሚያስተዳደሩ ሴቶች ቁጥር እያደገ ነዉ።የእድገቱ ደረጃ፤ እድገቱን ለማገዝ የሚያስፈልገዉ ድጋፍና ፖሊሲ፤ ፖሊሲዉን ገቢር ለማድረግ ያለዉ ፍላጎት ግን አሁንም አነጋጋሪ ነዉ።ዋና ዋኖቹን እያነሳን እንነጋገራን 3 እንግዶች አሉን።

ውይይቱን ከዚህ በታች በድምፅ ያገኙታል።

ነጋሽ መሀመድ

ልደት አበበ