1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያዉያን ባህላዊ ምግብ ቤቶች በጀርመን

ሐሙስ፣ ጥቅምት 29 2005

ከሀገር ወጥቶ የሚኖር ኢትዮጵያዊ የሀገሩን ባህል ይዞ፣ የአደገበትን ቀየ፤ የቤተሰብ የጎረቤት የጓደኛ ማስታወሻን፤ በሙዚቃ፣ በአልባሳት፣ አልያም በፎቶ ይዞ ፤ በሚኖርበት ባዕድ አገር፤ የሀገሩን ናፍቆት፤ ባህል፤ በትዝታ ማብሰልሰሉ ፤ አልፎም ለሌላዉ ወገን ማሳየቱ እና ማዉሳቱ አይቀሪ ነዉ።

https://p.dw.com/p/16fed
ምስል DW

ከሀገር ወጥቶ  የሚኖር ኢትዮጵያዊ የሀገሩን ባህል ይዞ፣  የአደገበትን ቀየ፤ የቤተሰብ የጎረቤት የጓደኛ ማስታወሻን፤ በሙዚቃ፣ በአልባሳት፣ አልያም በፎቶ ይዞ ፤ በሚኖርበት ባዕድ አገር፤ የሀገሩን ናፍቆት፤ ባህል፤ በትዝታ ማብሰልሰሉ ፤ አልፎም ለሌላዉ ወገን ማሳየቱ እና ማዉሳቱ አይቀሪ ነዉ። ጤና ይስጥልኝ አድማጮች እንደምን ሰነበታችሁ፤ ዓመት በአልም ሲመጣ  እንደ አደገበት እንደ ሀገሩ ባህል፤ ከሀገር ልጅ ተሰባስቦ በማክበር፥ አመት ያድርሰን ብሎ መለያየቱንም ባህሉ አድርጎታል። ከዝያም አለፍ ሲል የሀገር ቤት ትዝታን ይበልጥ ለማጉላት በርካታ ኢትዮጵያዉያንንም ለመገናኘት፤ ወደ ኢትዮጵያ የባህል ምግብ ቤቶች ጎራ የማለቱን ልምድ አዳብሮአል።  እዚህ ራድዮ ጣብያች ከሚገኝበት ከተማ ሰላሳ ኮሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘዉ በኮለኝ ከተማ ዉስጥ የኢትዮጳያን ባህላዊ የምግብ አይነቶች የሚያስተዋዉቁ የምግብ ቤቶች እና የእንጀራ እና በርበሪ መሸጫ መደብሮች መካከል  ሰላም የምግብ ቤት፤ ፋሲካ የኢትዮጵያ ምግብ ቤት፣ እና ብሉ ናይል ባህላዊ ምግብ ቤቶች ተጠቃሽ ናቸዉ። ምግብ ቤቶቹ የኢትዮጵያዊነትን ገላጭ ስም ይዘዉ፤ ከቅም ቅም አያቶቻችን በወረስነዉን የምግብ አሰራር ሞያ የተከሸነዉን የተለያየ ምግብ እና የመጠጥ አይነት፤ ለምዕራባዉያኑ ጎብኝዎቻቸዉ ሲያቀርቡ፤  የኢትዮጵያን ታሪክ በመግለጽ፤ ባህላዊ መስተንግዶን በማሳየት፣ የሀገርን ባህል ያስተዋዉቃሉ፤ ኢትዮጵያንም እንዲጎበኙ ይጋብዛሉ። በዚህ አኳያ እዚሁ ራድዮ ጣብያችን አካባቢ በሚገኘዉ በኮለኝ ከተማ ፋሲካ የኢትዮጵያ ባህል ምግብ ቤት አንዱ ሲሆን  በለቱ ዝግጅታችን ፋሲካ ምግብ ቤት ጎራ ብለን የኢትዮጳያ ባህላዊ ምግቦችን በመሶብ አስቀርበን፤ ቡና አጫጭሰን ምግብ ቤቱን እና ጎብኝዎችን አነጋግረን ነበር። ራልፍ  ቪገንድ ይባላሉ፤ በምግቤቱ የተዋወቅ ናቸዉ ጀርመናዊ።  በወንጌላዊት ቤተክርስትያን ስር ለልማት ስራ ከባለቤታቸዉ ጋር ወደ ኢትዮጵያ ሄደዉ ወደ አስራ ሶስት አመት ግድም ኖረዋል። በዚህም ምክንያት ነዉ  አማረኛን ጠንቅቀዉ የሚናገሩት። ከኢትዮጳያ ከተመለሱ አራተኛ አመታቸዉን እንደያዙ የሚናገሩት ራልፍ፤ የኢትዮጵያን ባህላዊ ምግብ ለመብላት በኮለኝ የሚገኘዉን የፋሲካ ምግብ ቤትን በየግዜዉ ይጎበኛሉ።  የ 2000 ዓመት ታሪክ እንዳላት በሚነገርላትና አንድ ሚሊዮን ነዋሪ በሚገኝባት በኮለኝ ከተማ ከሚገኙት የኢትዮጵያዉያን ባህላዊ ምግብ ቤቶች መካከል፤ ፋሲካ ምግብ ቤት ዘንድሮ የተከፈተበትን አስረኛ ዓመት በማክበር ላይ ይገኛል። ምግብ ቤቱን ከፍተዉ ሲገቡ የምግቡ እና የቡናዉ መዓዛ እንዲሁም በምግብ ቤቱ ከተሰቀለዉ የኢትዮጵን ባህል ገላጭ ከሆነዉ ስዕልና ባህላዊ ቁሳቁስ  ጋር ኢትዮጵያ የገቡ ያህል ይሰማል። የምግብ ቤቱ ባለቤት አቶ ዳዊት ደጀኔን አግኝተን  የምግብ ቤት ስራን እንዴት እንደ ጀመሩ አጫዉተዉናል። በጀርመን የሚገኙ የኢትዮጵያ ባህላዊ ምግብ ቤቶች የአገርን ባህል በማስተዋወቁ ረገድ እያደረጉ ያሉት እንቅስቃሴ ይበል የሚያሰኝ ነዉ። በኮለኝ ከተማ የሚገኘዉ እና የተመሰረተበትን አስረኛ አመት በማክበር ላይ ያለዉ ፋሲካ ምግብ ቤትም ኢትዮጵያን አንግቦ ዳግም አስር አስር አመትን ጨምሮ ፈረንጅን በጋራ በማዕድ መብላት እንድያሳይ በመመኘት የለቱን ቅንብሪን አጠናቅቄያለሁ አዜብ ታደሰ ነኝ። ሙሉዉን ቅንብር ያድምጡ!    

Fasika äthiopisches Restaurant in Köln
ምስል DW

 አዜብ ታደሰ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ