1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያዉያን ተቃዉሞ በለንደን

ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 27 2008

የብሪታንያ መንግሥት ለኢትዮጵያ የሚሠጠዉን ዕርዳታ እንዲያቋርጥ ብሪታንያ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ዛሬ በሠልፍ ጠየቁ።በብሪታንያ የኦሮሞ ሴቶች ማሕበር በጠራዉ የተቃዉሞ ሠልፍ ላይ የተገኙ ኢትዮጵያዉያን እንደሚሉት «የራሱን ዜጎች የሚገድል» ላሉት ለኢትዮጵያ መንግሥት ብሪታንያ ርዳታ መስጠት አይገባትም።

https://p.dw.com/p/1HZJ6
Großbritannien Symbolbild Olympische Spiele in London Big Ben und Flagge
ምስል Reuters

[No title]

ሠልፈኞቹ የኬንያ መንግሥት ከኢትዮጵያ ሸሽተዉ ሐገሩ የገቡ ስደተኞችን ለኢትዮጵያ መንግሥት አሳልፎ ሰጥቷል፤ የብሪታንያዉ ማሰራጫ ጣቢያ BBC ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚፈፀመዉን በደል ተከታትሎ አልዘገበም በማለትም ወቅሰዋል።የኢትዮጵያ መንግሥት የተቀናጀ ማስተር ፕላን ያለዉን ዕቅድ በተቃወሙ ሰዎች ላይ የወሰደዉን እርምጃ በመቃወም ለንደን ዉስጥ የአደባባይ ሠልፍ ሲደረግ በሰወስት ሳምንት ዉስጥ የዛሬዉ 3ኛዉ ነዉ።ነጋሽ መሐመድ የለንደን ወኪላችን ድልነሳ ጌታነሕን አነጋግሮታል።

ድልነሳ ጌታነሕ

ነጋሽ መሐመድ

ማንተጋፍቶት ስለሺ