1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያዊው ፎቶግራፍ አንሺ እርምጃ፣

ዓርብ፣ መጋቢት 7 2004

በሊባኖስ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያት ላይ የሚፈጸመውን ይግፍ እርምጃ በተለይም አንዲት ወጣት በጠራራ ፀሐይ በሊባኖሳውያን እንደበግ እየተጎተተችና እየተደበደበች ዘግናኝ ድርጊት ከተፈጸመባት በኋላ ፣ ህይወቷን በገዛ እጇ አጠፋች መባሉ በዓለም ዙሪያ

https://p.dw.com/p/14Lx5
ምስል Fotolia/Virste


በሊባኖስ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያት ላይ የሚፈጸመውን ይግፍ እርምጃ በተለይም አንዲት ወጣት በጠራራ ፀሐይ በሊባኖሳውያን እንደበግ እየተጎተተችና እየተደበደበች ዘግናኝ ድርጊት ከተፈጸመባት በኋላ ፣ ህይወቷን በገዛ እጇ አጠፋች መባሉ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን  እጅግ ማሳዘኑና ማናደዱ አልቀረም። ለብሔራዊ ውርደት ምልክት ሰጪ ነው የተባለውን እንዲህ ዓይነቱን ድርጊት እንዴት ነው መቃወምና ማስቆም የሚቻለው? ሁኔታው፣ ኢትዮጵያውን ዜጎችን በመላ የሚመለከት ነው በሚባልበት በዚህ ወቅት፤ በለንደን ኑዋሪ የሆኑት የቀድሞው ንጉሠ-ነገሥት አፄ ኃይለ ሥላሴ ፎቶግራፍ አንሺ የነበሩት አቶ ሽመልስ ደስታ ሊባኖስ ውስጥ በኢትዮጵያውያት ላይ የሚፈጸመውን  አሰቃቂ ተግባር በመቃወም ከ 46 ዓመታት ገደማ በፊት ከሊባኖስ መንግሥት የተሰጣቸውን የክብር ዲፕሎማና የክብር ኒሻን እንደሚመልሱ አስታውቀዋል። ድልነሣ ጌታነህ አቶ ሽመልስ ደስታን አነጋግሮ የሚከተለውን ዘገባ ልኮልናል።

ድልነሳው ጌታነህ

ተክሌ የኋላ