1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያውያን ስሞታ ከሳዉዲ እሥር ቤት

ሰኞ፣ የካቲት 24 2006

በስዑዲ ዐረቢያ በተለያዩ አሠሪዎች ተቀጥረው ይሠሩ የነበሩ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ፤ ባለፈው ኅዳርና ታኅሣሥ፣ በሕጋዊ የሥራና የመኖሪያ ፈቃድ ሰበብ ፤ በፖሊስና በጋጠ ወጥ ወጣቶች ፤ ማዋከብ ፤ ግድያና ድብደባ ፤ አስገድዶ መድፈርና የመሳሰሉ

https://p.dw.com/p/1BIoi
Saudi Arabien Riad Unruhen
ምስል AFP/Getty Images

ዘግናኝ እርምጃዎች ከተወሰዱባቸው በኋላ ፣ በሺዎች የሚቆጠሩ፣ ሕይወታቸውን ለማትረፍ ሲሉ ንብረታቸውን በቅጡ ሳይሰበሰቡ ወደ ትውልድ ሃገራቸው መመለሳቸው የሚታወስ ነው። ገሚሱ በተለያዩ ምክንያቶች ገና እንዳልተመለሱ ታውቋል። «የሥራ ፈቀድ የነበረን ነን፣ ሆኖም ፣ መመለስ ፈልገን ከመንግሥት በኩል ትብብር አልተደገልንም በማለት የሚያማርሩ ኢትዮጵያውያን ፣ ዛሬ የተቃውሞ ሰልፍ ከመደረጉ በፊት ፤ በሳምንቱ ማለቂያ ላይ ፣ ከዚያው ከስዑዲ ዐረቢያ ከጂዳ ፤ እሥር ቤት ከ SMSም ሌላ በስልክ እንዲህ ነው ብሶታቸውን የገለጡልን።

ተክሌ የኋላ

ኂሩት መለሰ