1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያውያን ስደትና መፍትሔዎቹ

እሑድ፣ ሚያዝያ 13 2005

ለተሻለ ህይወት አገር ጥለው ወጥተው፣ እንደ እቃ በደላሎች የሚሸጡ፣ ገንዘብ ካላመጣችሁ እየተባሉ የሰውነት አካላቶቻቸው ላይ ጉዳት የሚደርስባቸው፣ የግድያ ዛቻ የሚሰነዘርባቸው ብሎም የሚገደሉት ቁጥር ቀላል አይደለም ። ህገ ወጥ እየተባሉ በባዕድ አገር እስር ቤቶች የሚሰቃዩትም እንዲሁ በርካታ ናቸው ።

https://p.dw.com/p/18Je2
ምስል AP


የኢትዮጵያውን ስደተኞች ቁጥር እየጨመረ በመሄድ ላይ ባለበት በአሁኑጊዜ በየሄዱበት የሚገጥሟቸው ችግሮችም የዚያኑ ያህል ከፍ ብለዋል ። በተለይ ወደ ጎረቤት ና አረብ ሃገራት የሚሰደዱት በጉዞ ወቅት እንዲሁም በተሰደዱባቸው አካባቢዎች እጅግ ዘግናኝ በደሎች እንደሚፈፀሙባቸው በተለያዩ አጋጣሚዎች ይናገራሉ ። ለተሻለ ህይወት ሃገር ጥለው ወጥተው ፣ እንደ እቃ በደላሎች የሚሸጡ ፣ ገንዘብ ካላመጣችሁ እየተባሉ የሰውነት አካላቶቻቸው ላይ ጉዳት የሚደርስባቸው ፣ የሚገደሉ ፣ የግድያ ዛቻ የሚሰነዘርባቸው ቁጥር ቀላል አይደለም ። ህገ ወጥ እየተባሉ በባዕድ ሃገር እስር ቤቶች የሚሰቃዩትም እንዲሁ በርካታ ናቸው ። እየተባባሰ የሄደው የኢትዮጵያውያን ስደትና መፍትሔዎቹ የእንወያይ የመነጋገሪያ ርዕሰ ነው ።

ሂሩት መለሰ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ