1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ተቃውሞ በብራሰልስ እና በጆሀንስበርግ

ዓርብ፣ ነሐሴ 13 2008

የአውሮጳ ህብረትም ለኢትዮጵያ መንግሥት የሚሰጠውን እርዳታ ዳግም እንዲመረምር ለህብረቱ የውጭ ጉዳዮች ሃላፊ ፌደሪካ ሞጎሮኒ በሰጡት ደብዳቤ ጠይቀዋል ።

https://p.dw.com/p/1Jlv5
Südafrika Äthiopien Solidaritätsbekundung
ምስል DW/M. Ayele

[No title]

ኢትዮጵያውያን ዛሬ በአውሮፓ ህብረት መቀመጫ ብራሰል በኢትዮጵያ በአማራ እና በኦሮምያ ክልሎች ለሚካሄዱት ተቃውሞዎች ድጋፋቸውን የገለፁበት ሰላማዊ ሰልፍ አካሄዱ ። ሰልፈኞቹ የኢትዮጵያ መንግሥት ባለፈው ሰሞን በሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፈኞች ላይ የወሰዳቸውን እርምጃዎች አውግዘው የአውሮጳ ህብረትም ለኢትዮጵያ መንግሥት የሚሰጠውን እርዳታ ዳግም እንዲመረምር ለህብረቱ የውጭ ጉዳዮች ሃላፊ ፌደሪካ ሞጎሮኒ በሰጡት ደብዳቤ ጠይቀዋል ። በደቡብ አፍሪቃ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ደግሞ መንግሥት በዜጎቹ ላይ ይፈጽማል ያሉትን የሰብዓዊ መብት ረገጣ በመቃወም ትናንት ጆሃንስበርግ ውስጥ ሰላማዊ ሰልፍ አካሂደዋል ። በሰላማዊ ሰልፍ ላይ ከተሰሙት መፈልክሮች መካከል ፣« የኦሮሞን ተቃውሞ እንደግፋለን» ፣ «የአማራን ተቃውሞ እንደግፋለን» የሚሉት ይገኙበታል ። የሰልፉ ተካፋዮች ጆሃንስበርግ ለሚገኘው ወኪላችን መላኩ አየለ እንደተናገሩት የሰልፉ ዓላማ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የሚፈጽመው የመብት ረገጣ እንዲቆም መጠየቅ ፣ እንዲሁም ችግሩን ለደቡብ አፍሪቃ መንግሥት እና እዚያ ለሚገኙ ዲፕሎማቶች ማሳወቅ ነው ። የብራሰልሱን ሰልፍ የተከታተለው የብራሰልሱ ዘጋቢያችንን ገበያው ንጉሴን በስልክ አነጋግሬዋለሁ ። ስለጆሀንስበርጉ ሰልፍ ደግሞ መላኩ አየለ ዘገባ ያቀርብልናል ።

ገበያው ንጉሴ
መላኩ አየለ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ
ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ