1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያውያን የስደት አዙሪትና መፍትሄው

እሑድ፣ ሐምሌ 19 2007

በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በአደገኛ የባህር ጉዞ ለመጀመሪያ ጊዜ እንዲሁም እንደገና እየተመለሱ የመን እየገቡ ነው ። ከመካከላቸው ከዚህ ቀደም ወደ ተባረሩበት ወደ ሳውዲ አረቢያ ለመሄድ የሚጠባ በቁም ይገኙበታል ።

https://p.dw.com/p/1G4RH
Screenshot Video Human Rights Watch Afrikanische Flüchtlinge im Jemen
ምስል Human Rights Watch/Yotutube

የኢትዮጵያውያን የስደት አዙሪትና መፍትሄው


ውጊያ በሚካሄድባት የመን የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን የማስወጣቱ ስራ ቀጥሏል ።የኢትዮጵያ መንግሥት ና ዓለም ዓቀፉ የስደተኞች ጉዳይ ድርጅት IOM እስካሁን 5871 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሃገራቸው መመለሳቸው ተዘግቧል ።በሌላ በኩል ኢትዮጵያውያኑን ወደ ሃገራቸው የመመለሱ ጥረት በቀጠለበት በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በአደገኛ የባህር ጉዞ ለመጀመሪያ ጊዜ እንዲሁም እንደገና እየተመለሱ የመን እየገቡ ነው ። ከመካከላቸው ከዚህ ቀደም ወደ ተባረሩበት ወደ ሳውዲ አረቢያ ለመሄድ የሚጠባ በቁም ይገኙበታል ። ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ከየመን የመመለሱ ጥረትና የኢትዮጵያውያን የስደት አዙሪት የዛሬው እንወያይ የመነጋገሪያ ርዕስ ነው ።

ኂሩት መለሰ

አዜብ ታደሰ