1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያው የምርጫ ዝግጅትና፣ የአውሮፓው ኅብረት የምርጫ ታዛቢዎች መሪ፣

ዓርብ፣ ግንቦት 6 2002

የአውሮፓው ኅብረት ፣ የዘንድሮውን የኢትዮጵያ ምርጫ ለመታዘብ 150 ልዑካን የሚያሠማራ ሲሆን፣ 90 ገደማ የሚሆኑት የቅድመ-ምርጫውን ሂደት ለመከታተል ከተላኩ ቆይቷል።

https://p.dw.com/p/NOWu
ምስል DPA

ቀሪዎቹ፣ ምርጫው ሊጀመር አቅራቢያ ወደዚያ ይጓዛሉ። የ 150 ው ታዛቢ ልዑካን መሪ፤ ኔደርላንዳዊው የአውሮፓ ኅብረት አባል ታይስ በርማን ደግሞ የፊታችን ሰኞ ይሆናል አዲስ አበባ የሚገቡት። የብራሰልሱ ዘጋቢአችን ፣ ገበያው ንጉሤ፣ ክግራና ከቀኝ እየተሰነዘሩ ስላሉ ወቀሳዎች ከአንድ እጩ ተወዳዳሪ ጋር በጠቅላላ 4 የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት፣ እንዲሁም አንድ ፖሊስ ስለመገደላቸው መገለጡ፣ የፈጠረውን የፖለቲካ ውጥረትና አሳሳቢነት፣ ሌሎች ተዛማጅ ጉዳዮችንም በማንሣት አነጋግሮአቸዋል።

ገበያው ንጉሤ

ተክሌ የኋላ

ሒሩት መለሰ