1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ሁኔታ እና የአሜሪካን ጥቅም 

ሐሙስ፣ የካቲት 8 2010

የአሜሪካ የስለላ ድርጅቶች በአረብ ባህረ ሰላጤ አካባቢ በሳዑዲ አረቢያ እና በኢራን መካከል በእጅ አዙር የሚካሄደው ዉጊያ፤ እንዲሁም በኬንያ እና ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚታየው የሕዝብ ቁጣና እና ተቃዉሞ የአሜሪካንን ብሔራዊ ጥቅሞች ስጋት ላይ የሚጥሉ ናቸዉ ብለዋል።

https://p.dw.com/p/2sldg
USA Kapitol in Washington
ምስል Getty Images/AFP/S. Loeb

የኢትዮጵያ ሁኔታ እና የአሜሪካን ጥቅም

የዩናይትድ ስቴትስ ብሔራዊ የስልላ መሥሪያ ቤት በያዝነው ጎርጎሪዮሳዊ ዓመት 2018 የሀገሪቱ ብሔራዊ ጥቅሞችን ለአደጋ የሚያጋልጡ ያላቸውን ጉዳዮች ይፋ አደረገ። እንደ ድርጅቱ በአረብ ባህረ ሰላጤ አካባቢ በሳዑዲ አረቢያ እና በኢራን መካከል በእጅ አዙር የሚካሄደው ዉጊያ፤ እንዲሁም በኬንያ እና ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚታየው የሕዝብ ቁጣና እና ተቃዉሞ የአሜሪካንን ብሔራዊ ጥቅሞች ስጋት ላይ የሚጥሉ ናቸዉ። የአረብ ባህረ ሰላጤዉ አካባቢ ዉጥረት ለኢትዮጵያስ ምን ማለት ነው? ከዋሽንግተን ናትናኤል ወልዴ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።

ናትናኤል ወልዴ

ሸዋዬ ለገሠ