1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ልዑካን በጀርመን

ሰኞ፣ መጋቢት 30 2011

በኢትዮጵያ የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ሂደቱን ለማጠናከር እና ለመጭው ምርጫ ስኬት የጀርመን መንግሥት እና ዓለም አቀፍ የጀርመን ግብረሰናይ ድርጅቶች ድጋፋቸውን እንደሚያጠናክሩ ተገለፀ። የጀርመን መንግሥት ባዘጋጀው የተፎካካሪ ፓርቲ ተጠሪዎች እና የኢትዮጵያ መንግሥት ተወካዮች የተካተቱበት የልዑካን ቡድን በጀርመን የሥራ ጉብኝት አድርጓል።

https://p.dw.com/p/3GTAr
Äthiopien Deutsche Botschaft Gäste verschiedener äthiopischer Parteien
ምስል German Embassy Addis Ababa

ወ/ሪት ብርቱካን ስለጉብኝቱ ውጤት እና ስለመጪው ምርጫ ዝግጅት»

 የቡድኑ አባል የሆኑት የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ በተለይ ለ ዶይቼ ቬለ (DW) እንደገለጹት የጀርመን መንግሥት ከአሁን ቀደም በአውሮጳ ሕብረት በኩል ለአገሪቱ የሚሰጠውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጧል። የኢትዮጵያ የምርጫ ሕግ ማሻሻያ አዋጅ መጽደቅንም ተከትሎ ሕጋዊ ምዝገባ ሳያካሂዱ እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ፓርቲዎች ላይ ቁጥጥር እንደሚጀመርም ወይዘሪት ብርቱካን አመልክተዋል። የፖለቲካ ፓርቲዎች የፋይናንስ ድጋፍ የኮታ ድልድልን በተመለከተም በኅብረተሰቡ ውስጥ ጥሩ መሠረት ያላቸው እና የዲሞክራሲያዊ ሂደቱን በደንብ ሊያግዙ የሚችሉ ድርጅቶች የተሻለ ድጋፍ እንደሚያገኙም ጠቁመዋል። ዝርዝሩን እንዳልካቸው ፈቃደ አጠናቅሮታል::

እንዳልካቸው ፈቃደ

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ