1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ሕገ-መንግስትና ገቢራዊነቱ

ሰኞ፣ ታኅሣሥ 1 2005

የወጣቶቹን ቀና ጥሪ፥ የተቃዋሚ ፖለቲከኞችን ገንቢ ትችት፥ የባለሙያዎችን ጠቃሚ ምክር፥ የሕዝብን ሰላማዊ ጥያቄ ለማድመጥ፥ ሰልፈኛዉ እንዳለዉ ያሉ አልመሰሉም።ወይም አልፈለጉም።ጠሪ፥ ተቺ፥ መካሪ፥ ጠያቂዎችን ለማጣጣል ግን በርግጥ አሉ።ጠቅላይ ሚንስትር ሐይለማርያም ደሳለኝ።

https://p.dw.com/p/16zVV
Die römische Göttin der Gerechtigkeit Justitia steht mit einer Waage und einem Richtschwert in den Händen auf dem Gerechtigkeitsbrunnen am Römer in Frankfurt am Main am 07.12.2007. Die Göttin aus der römischen Mythologie gilt als Wahrzeichen und Symbol der Justiz und der Gerechtigkeit. Foto: Wolfram Steinberg +++(c) dpa - Report+++
ፍትሕምስል picture alliance/dpa

10 12 12

ብዙም፥-አንድም ናቸዉ።

   
ወጣቶቹ

የሕግ ባለሙያዎቹ


«ገዢዉ ፓርቲ ሕገ-መንግሥቱን አያከብርም»


ፖለቲከኛዉ።


ከሕገ-መንግሥቱ የአንዱን አንቀፅ ቁጥር ያነገበዉ ሕዝብ ደግሞ ጠየቀ።እሳቸዉ የወጣቶችን ቀና ጥሪ፣ የባለሙያዎችን ጠቃሚ ምክር፣ የፖለቲከኞን ገንቢ ትችት የሕዝብን ሰላማዊ ጥያቄ ለማድመጥ ሰልፈኛዉ እንዳለዉ ያሉ አይመስልም።ወይም አልፈለጉም።ግን አለሁ-አሉ።ተናገሩም።
              
«ከሕገ-መንግሥቱ በሕዋላ---- ሕዝባችን በሥርዓቱ በጣም ረክቷል።»


ጠቅላይ ሚንስትር ሐይለማርያም ደሰላኝ።

ዛሬ የዓለም የሰብአዊ መብት ቀን ነዉ።ባለፈዉ ቅዳሜ የኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥት የፀደቀበት አስራ-ስምተኛ አመም።አጋጣሚዉ መነሻ፥የተቃርኖዉ ምክንያት ማጣቃሻ ፖለቲካዉ እንድምታዉ መድረሻችን ነዉ ላፍታ አብራችሁኝ ቆዩ።እሳቸዉ እና እነሱ ምናልባትም የአያት-ይሕ ቢቀር የአባትና ልጅ የእድሜ ክፍተት የሚያለያያቸዉ የሩቅ ለሩቅ ዘመን ዉልዶች ናቸዉ።እሳቸዉ በእግረ-ሰፊ ሱሪ፣ በታኮ ትልቅ ጫማ በሚዘነጥበት፣ ዘመን ወጣትነትን የተሰናበቱ፣ ዶክተርነትን የጨበጡ፣ የኮሚኒስት-ካፒታሊስ ፖለቲካዉ ፍልስፍና በናኘበት ዘመን ፖለቲካን የተቀየጡ ናቸዉ።ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ።

«ኢሕአዴግ ለሕዝብ ፍላጎት ደንታ የማይሰጥ ድርጅት ነው፡፡በሕገ-መንግሥቱ የተረጋገጡትንና በአንቀጽ 29፣ 30: 31፣ እና 38 የተዘረዘሩትን መብቶች አፍኖል፡፡ገዢው ፓርቲ ሕገ-መንግሥቱን አያከብርም።፡» እያሉ ፃፉ በቀደም።


ከእነሱ አብዛኞቹ ሃያዎቹን ያልጨረሱ ተማሪ ወይም ስራን ከጥቂት አመታት በላይ የማያዉቁ ወጣቶች ናቸዉ።የፌስ-ቡክ፣ የቲዉተር ዘመን ዉልዶች።አንጋፋዉ ፖለቲከኛ እንደሚያዉቁት በወረቀት ሲፅፉ፥ ወጣቶቹ እንደዘመኑ ፊሊጥ በአምደ-መረብ ዘመቱ።«ሕገ-መንግሥቱ ይከበር።» እያሉ
                    
ሰወስተኞቹ በእድሜም በሙያም፣ ከሁለቱም አይገጥሙም።ወይም የሚገጥሙ አይመስሉም። በአዛዉንቱ ምሁር ፖለቲከኛ እና በወጣቶቹ መካካል ያለዉን የዘመን ክፍተት ለማገኛኘት ግን የጎልማሳነት እድሚያቸዉ፥ እዉቀት ሙያቸዉ ጥሩ ድልድይ ያስመስላቸዋል።

በፖለቲካዉ ርዕዮት እንደ ወጣቶቹ ገለልተኛ ሆነዉ ከሽማግሌዉ ይርቃሉ።ሁለቱም የሕግ አዋቂዎች ናቸዉ።አንደኛዉ ዶክተር መሐሪ ታከለ።

ሁለተኛዉ አቶ ተማም አባቡልጋ።በአሸባሪነት የተከሰሱት የሙስሊም መሪዎችና ተባባሪዎቻቸዉ ጠበቃ ናቸዉ።
                  
እና እድሜ፥ እዉቀት፥ የፖለቲካ ዝንባሌ የሚያራርቃቸዉ ሰወስቱም ወገኖች የኢትዮጵ ሕገ-መንግሥት ከመከበሩ ይልቅ በመጣሱ አንድ እዉነት አንድ-ሆኑ።

ካለፈዉ ዓመት ጥር ጀምሮ መንግሥት በሐይማኖታዊ ጉዳያችን ጣልቃ ገብቷል በማለት ሲፈቀድላቸዉ ከራሱ ከመንግሥት ጋር የተደራደሩት፥ ሲከለከሉ፥ በየመሳጂዱ የጮኹት ሙስሊሞች ጥያቄም ደጋግመዉ እንዳስታወቁት አንድ ነዉ።ሕገ-መንግሥቱ ይከበር።

ሙስሊሙን ወክለዉ ከመንግሥት ጋር ሲደራደሩ ከነበሩትና ከተወካቻቸዉ ጋር ከታደሙት ሃያ-ዘጠኙ ባለፈዉ ሐምሌ ታስረዉ፥ በአሸባሪነት ተወንጅለዋል።

የሙስሊሞቹ ተወካዮች ከታሰሩ፥ በአሸባሪነት ከተከሰሱ፥ ከአዲስ አበባ-እስከ ሐርቡ፥ ከደሴ እስከ አርሲ በየመስጂዱ የተሰበሰቡ ሙስሊሞች በፀጥታ አስከባሪዎች ባደባባይ እየተደበደቡ፥ ከታሰሩ፥ ከተጋዙ፥ መንግሥት ምርጫ ያለዉ ምርጫ ከተደረገም በሕዋላ ጥያቄ-ተቃዉሞዉ አላባራም።

ሕገ-መንግሥቱ የፀደቀበት አስራ-ስምተኛ ዓመት ከመታሰቡ ካንድ ቀን በፊት አንዋር መስጊድ የታደመዉ ሙስሊም፥ የሐማኖት ነፃነትን የሚጠይቀዉን የሕገ-መንግሥቱን አንቀፅ-ሃያ ሰባትን አንግቦ በሰወስት የፈረጅናቸዉን ወገኖችን አስተያየት ተጋራ።ሕግ አክባሪ-አስከባሪ መንግሥት የለም ወይ እያለም ጠየቀ።ዘመረም።
                
እሳቸዉ የወጣቶቹን ቀና ጥሪ፥ የተቃዋሚ ፖለቲከኞችን ገንቢ ትችት፥ የባለሙያዎችን ጠቃሚ ምክር፥ የሕዝብን ሰላማዊ ጥያቄ ለማድመጥ፥ ሰልፈኛዉ እንዳለዉ ያሉ አልመሰሉም።ወይም አልፈለጉም።ለሳቸዉ ለመንግሥታቸዉ፥ ለሐገር ሕዝባቸዉ የሚጠቀም ነዉን ለማድማጥ የሌሉት ወይም ያልፈለጉት፥ ጠሪ፥ ተቺ፥ መካሪ፥ ጠያቂዎችን ለማጣጣል ግን በርግጥ አሉ።ጠቅላይ ሚንስትር ሐይለማርያም ደሳለኝ።
                   
«እንደሚመስለኝ ይሕ የአናሳዎች ድምፅ ነዉ።የአብዛኞቹ ሙስሊሞች ድምፅ አይመስልም።የአብዛኞቹ ጥያቄ የአስተዳደር ሥርዓት እንዲኖራቸዉ ነበር።የራሳቸዉ የአስተዳደር ሥርዓት ሥርዓት።መንግሥት ከሐይማኖታዊ አስተዳደራቸዉ ጋር ምንም ግንኙነት የለዉም።»

ዶክተር መሐሪ እንደሚሉት ሕግ-ወይም ሕገ መንግሥት ሲወጣ በሥልጣን ላይ ያለ ሥርዓትን ግለሰብን፥ ወይም ቡድንን ብቻ አስቦ፥ ወይም መሠረት አድርጎ መሆን የለበትም።
           

ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ የሚመሩት የሕገ-መንግሥት አፅዳቂ ምክር ቤት ሕዳር ሃያ-ዘጠኝ ሺ ዘጠኝ መቶ ሰማንያ ሰባት የኢትዮጵያ ፌደራላዊት፣ ዴምክራሲያዊት ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥትን ሲያፀድቅ የያኔዎቹን ፖለቲከኞች፥ የሕግ አዋዊቂዎችና ተንታኖችን እኩል አስደስቶ ነበር ማለት በርግጥ ስሕተት ነዉ።

ይሁንና ዶክተር መሐሪ እንደሚሉት ሕገ-መንግሥቱ እስከዚያ ዘመን ድረስ የነበሩ የኢትዮጵያዊያንን መሠረታዊ የፍትሕ ጥያቄዎች ለመመለስ ሕገ-መንግሥቱ ጥሩ ሰነድ ነዉ።
                     
ጥሩዉ ሰነድ ለያኔዎቹ ሕፃናትና ወጣቶች፥ ለወደፊቱ ትዉልድም የተሻለ ፍትሕ፥ ነፃነት፥ እኩልነት የሰፈናባት ኢትዮጵያን ለመፍጠር ይበጃል፥ ያስችላል የሚል እምነት ነበር።ባለፉት አስራ-ስምት አመታት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ የገዢዉን ፓርቲ መስመር ተከትለዉ ከሚንስርነት እስከ ፕሬዝዳትነት ደርሰዉ፥ ከገዢዉ ፓርቲ ተነጥለዉ እንደ ግል ፖለቲከኛ ከምር ቤት እንደራሴነት ወደ ተቃዋሚ ፓርቲ መሪነት ተለዉጠዋል።

በዚሁ ዘመን በሕገ-መንግሥቱ የተደነገገዉን መብት በመጠቀም ለመደራጀትና ለማደራጀት የሞከሩ በርካታ ተቃዋሚ ፖለቲከኞች፥ የሙያና የሠረተኛ ማሕበራት ተወካዮች፥ ለፍርድ ቤት ነፃነት የተሟገቱ ዳኞች ሳይቀሩ አንድም ታስረዋል፥ አለያም ተሰደዋል ወይም ከስራ ተወግደዋል።በምርጫ የተወዳደሩ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች፥ ለተቃዉሞ ያንገራገሩ ወጣቶች፥ መንግሥትን ለመተቸት የሞከሩ ጋዜጠኞች «ሕገ-መንግሥቱን ለመናድ» በሚል ወንጀል ታስረዋል።ተቀጥተዋል።ተሰደዋል።ተቋማት ተዘግተዋል።ማሕበራት ተበትነዋል።

እዚሕ ቦን ይማር የነበረ ኢትዮጵያ ለደቡብ አፍሪቃዊ ባልጀራዉ የኢትዮጵያ የቀን አቆጣጠር ከጎርጎሮሳዉያኑ በሰባት ወይም በስምንት አመት እንደሚያንስ ይነግረዋል።«እኸ» አለ አሉ ደቡብ አፍሪቃዊዉ «ኢትዮጵያዉያን፥ እየሱስ ክርስቶስ መወለዱን የሰሙት ከስምት ዓመት በኋላ ነዉ-ማለት ነዉ?» ብሎ ኢትዮጵያዊ ባልንጀራዉን ጠየቀዉ።ወይም አሾፈበት።

ዩናይትድ ስቴትስ አል-ቃኢዳን በአሸባሪነት የፈረጀችዉ በ1991 ነበር።በ1994 ኒዮርክና ዋሽግተን አል-ቃኢዳ እንዳዘመታቸዉ በሚታመን ወጣቶች ከተመቱ በሕዋላ ደግሞ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትን ጨምሮ አብዛኛዉ ዓለም ያን ድርጅት በአሸባሪነት ፈርጆታል።

የኢትዮጵያ መንግሥት አል-ቃኢዳን እና አሸባብን በአሸባሪነት ለመፈረጅ አንድም ደቡብ አፍሪቃዊዉ ተማሪ እንዳሾፈዉ ከተቀረዉ ዓለም በሕዋላ ስምንት ዓመት መጠበቅ፥ አለያም ሁለቱን አሸባሪ ድርጅቶች የኦነግ፥ የኦብነግ እና የግንቦት ሰባት መናጆ የሚያደርግበትን አጋጣሚ መፈለግ ነበረበት።

በ2001 በወጣዉ የፀረ-ሽብር ሕግ መሠረት፥አምስቱ ድርጅቶች ሐምሌ ሁለት ሺሕ ሰወስት በአሸባሪነት ተፈረጅዋል።ከዚያ በሕዋላ የመብት ተሟጋቾች እንደሚሉት ከርዮት-እስከ እስክንድር ያሉ ጋዜጠኞችን፥ ከኦልባና እስከ አንዱ ዓለም፥ ያሉ ፖለቲከኞች፥ ከመስሊም መሪዎች እስከ ሚንስትር ባለቤት ያሉ ተሟጋቾችን ለማሰርና በአሸባሪነት ለመወነጀል ብዙዎች እንደሚሉት ሕገ-መንግሥቱን የሚቃረነዉ የፀረ-ሽብር አዋጅ አልፋ-ወኦሜጋ ሆነ።ሺዎች ታስረዋል።ተከሰዋል።ተፈርዶባቸዋልም።

ጠቅላይ ሚንስትር ሐይለ ማርያም ግን እሰረኛ የለም ባይ ናቸዉ።«እስር ቤት ዉስጥ የሚማቅቁ ፖለቲከኞች የሉም።ቁጥር-አንድ።እስር ቤት ዉስጥ የሚማቅቁ ሌሎች የፖለቲካ አቀንቃኞች የሉም።በመርሐችንና በአዕምሯችን በጣም ግልፅ ነን።የሐገሪቱን ሕግ የሚጥስ ማንኛዉም ሰዉ፥ ፖለቲከኛ ይሁን የመንግሥት አካል ሁሉም ከሕግ በታች ናቸዉ።»

የሕገ-መንግሥት አስራ-ስምንተኛ ዓመት ሲዘከርም ይሕን መሰሉ ተቃርኖ መደመጡ ነዉ-የወደፊቱም ከእስካሁኑ የበለጠ የማስጋቱ ነዉ-ፍራት ጭንቀቱ።ዶክተር መሐሪ ፍራቱን ለማስወገድ አብነት የሚሉት አላቸዉ።ሰሚ ይኖር ይሆን? ካለ ሲሆን ለማየት-መስማት ያብቃን።ለዛሬዉ ግን በቃን።ነጋሽ መሐመድ ነኝ ቸር ያሰማን።

Autor: Ludger Schadomsky Copyright: Ludger Schadomsky/DW Titel: Dr. Negasso Gidada Thema: Der ehemalige Staatspräsident und heutige Vize-Vorsitzender des Achtparteien-Oppositionsbündnisses „Medrek“ , Dr. Negasso Gidada, ist vor der Wahl ein gefragter Gesprächspartner Schlagwörter: Negasso Gidada, Medrek, Forum, Äthiopien 2010, Äthiopien Opposition, Ethiopia 2010, Wahl Äthiopien
ዶክተር ነጋሶምስል DW
Ethiopian state television announced on August 21, 2012 that Hailemariam Desalegn will be acting prime minister, after the death of Ethiopian Prime Minister Meles Zenawi.
ጠ/ሚ ሐይለማርያምምስል CC-BY-SA- World Economic Forum
Ethiopian students demonstrate outside Addis Ababa Tegbareed Industrial College in the capital's Mexico area., Tuesday, June 7, 2005. Police raided a technical college in Ethiopia's capital Tuesday, beating up students and firing rubber bullets on the second day of defiance of a government ban on demonstrations, witnesses said. Clashes between police and student demonstrators on Monday left a girl dead, seven people injured and hundreds arrested in protests against disputed election results that left parliament in the hands of the ruling party. (AP Photo)
1997 የተማሪዎች ተቃዉሞምስል AP
***Für mögliche Ergänzungen der Karte, wie z.B. andere Sprachen, zusätzliche Orte oder Markierungskreuz, wenden Sie sich bitte an infografik@dw-world.de (-2566), Außerhalb der Bürozeiten an bilder@dw-world.de (-2555).*** DW-Grafik: Per Sander 2011_03_10_Laender_Prio_A_B
Karte Äthiopien englisch

ነጋሽ መሐመድ

ሒሩት መለሰ










    









               




 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ