1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ መንግሥት ድጋፍ ማሰባሰቢያ

ረቡዕ፣ የካቲት 8 2009

ኢትዮጵያ የአሜሪካንን የፖለቲካ እና የዲፕሎማሲ ድጋፍ ለማግኘት ግፊት ወይም «ሎቢ» የማድረግ ሥራ ለሚያከናውንላት «SGR»ለተባለ ተቋም 1.8 ሚሊዮን ዶላር ለመክፈል መስማማቷ ተሰምቷል ።

https://p.dw.com/p/2XcRR
12.06.2013 DW Online Karten Basis Äthiopien Englisch

New MMT Beri.Wash. Ethiopia's lobby in US - MP3-Stereo

 ከአሜሪካን የውጭ ተቋማት ምዝገባ ደንብ ተገኝቷል በተባለው መረጃ መሠረት ስምምነቱ ከአንድ ወር በፊት ተፈርሟል። ገንዘብ የሚከፈለው ድርጅት ተግባርም ኢትዮጵያ የአሜሪካንን ድጋፍ እንድታገኝ የአሜሪካንን ባለሥልጣናት፣ ማግባባት ማሳመንን እና ግፊት ማደረግ ነው። ዶይቼ ቬለ ስለጉዳዩ ያነጋገራቸው ምሁራን የኢትዮጵያ መንግሥት በዚህ ዘዴ በሀገሪቱ በተነሱ አመጾች በምርጫ ግድፈቶች እና መሰል ችግሮች ሰበብ ከአሜሪካን በኩል ጠንካራ ተቃውሞ እንዳልገጠመው ተናግረዋል።  ዘዴው ሀገሪቱ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ለተለያዩ ሃላፊነቶች ለመመረጥ እንደረዳት ያስረዱት እነዚሁ ምሁራን በአዲሱ የአሜሪካን አስተዳደር ይህ መንገድ የሚሰራ እንደማይመስላቸው ገልፀዋል ። ስለጉዳዩ የተጠየቀው ዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ  ምንም የሚያውቀው ነገር እንደሌለ ለዶይቼ ቬለ ገልጿል ። 

መክብብ ሸዋ

ኂሩት መለሰ

አርያምተክሌ