1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ መንግሥት 206 መያዶች ዘጋ

Merga Yonas Bulaሐሙስ፣ ሐምሌ 28 2008

ኢትዮጵያ ዉስጥ ተመዝግበዉ የሚንቀሳቀሱ 4000 መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እንዳሉ የሚናገሩት የኢትዮጵያ የበጎ አድራጎትና ማህበራት ድርጅት (ኤጄንሲ)የህዝብ ግኑኝነትና ኮሙኒኬሼን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክቴር አቶ መስፍን ታደሰ፤ መስሪያ ቤታቸዉ በዚህ ዓመት 3574 ድርጅቶች ላይ ክትትል እንዳደረገ ለዶቼ ቬሌ ተናግረዋል።

https://p.dw.com/p/1Jbjn
Karte Ethiopia und Eritrea ENG

[No title]

ክትትሉን ተከትሎም የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት አዋጅ የሚጠይቀዉን አላሟሉም በተባሉት ላይ ርምጃዎች ተወስደዋል። እነዚህ 206 ድርጅቶች ቢዘጉም በዚህ ዓመት ለ187 አዳዲስ ድርጅቶች ፊቃድ እንደተሰጠ እና የ803ቱ ፍቃድ መታደሱንም አቶ መስፊን ይናገራሉ።

ለመያዶቹ መዘጋት የተሰጠዉ ምክንያት የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት አዋጅ የሚጠይቀዉን መመዘኛ ባለማሟላታቸዉ እና የገንዘብ እጥረት ስላጋጠማቸዉ ነዉ ቢባልም የተዘጉት ድርጅቶች አዋጁ ራሱ ገደብ የሚጥል እንደሆነና በዲሞክራሲና ማህባራዊ ጉዳዮች ላይ መስራት እንዳልቻሉ ይጠቅሳሉ።


የኢትዮጵያ በጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ማድረክ ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተለ መሁኑን የማድረኩ ሊቀመንበር አቶ ነጋሽ ተክሉ ተናግሮ ድርጅቶቹ መዘጋታቸዉ ለአገሪቱ ልማት ያደርጉት የነበረዉን አስተዋፅኦ ይጎዳዋል ይላሉ። በፖለትካ መብቶች ሳይሆን በማህበራዊ መብቶች ላይ አዋጁ መሻሻል አለበት ባይም ናቸዉ።

በድረ ገፃችን ላይም ከደረሱን አስተያየቶች ዲሞክራሲያዊና ማህባራዊ እንቅስቃሴዎች ላይ የሚሰሩበትን ድርጅቶች መዝጋት በአገርቱ ያለዉን የፖለትካ ቀዉስ ያባብሳል እናም ከማትወጣበት ችግር ዉስጥ ይከታታል ሲሉ አስተያየተቸዉን አጋርቶናል።

መርጋ ዮናስ

ነጋሽ መሃመድ