1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ማህበራዊ ተጠያቂነት ሽልማት

ረቡዕ፣ ጥቅምት 24 2008

በውኃ በመብራት በጤናና በመሳሰሉት አገልግሎቶች ውስጥ የታዩ ችግሮችን በማንሳት በድራማ መልክ እያቀረቡ ህዝቡ፤ ስለችግሩ መፍትሄ ለማግኘት መጠየቅ እንዳለበት አንቅተዉ ለውጤት አብቅተዋል የተባሉ ግለሰቦችና ተቋማት ተሸልመዋል።

https://p.dw.com/p/1GzZv
Karte Äthiopien englisch

የኢትዮጵያ ማህበራዊ ተጠያቂነት ፕሮግራም በምዕራፍ ሁለት ፕሮጀክት የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ዛሬ የኮሚኒኬሽን ወይም የግንኙነት አግባብ ሽልማት ሰጠ። ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ በተካሄደው ስነ ሥርዓት በውኃ በመብራት በጤናና በመሳሰሉት አገልግሎቶች ውስጥ የታዩ ችግሮችን በማንሳት በድራማ መልክ እያቀረቡ ህዝቡ፤ ስለችግሩ መፍትሄ ለማግኘት መጠየቅ እንዳለበት አንቅተዉ ለውጤት አብቅተዋል የተባሉ ግለሰቦችና ተቋማት ተሸልመዋል። ፕሮጀክቱ በፋይናንስና ኤኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ባለቤትነት በተለያዩ ለጋሾች ድጋፍ ነው የሚካሄደው። ዓላማውም ህብረተሰቡ በሚያገኘው የተለያየ አገልግሎት መብቱን አውቆ እንዲጠይቅና መፍትሄ እንዲሰጠው የሚያደርግ መሆኑን ቀጣዩ የወኪላችን የዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ዘገባ ያስረዳል።

የዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ኂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ