1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድና መኢአድ

ረቡዕ፣ መስከረም 12 2003

መኢአድ ዛሬ ባወጣዉ መግለጫዉ እንዳለዉ ድርጅቱ የመሠረተዉ ክስ ብይን ሳያገኝ ምርጫ ቦርድ ዉጤት ማወጁ ሕጋዊ ሒደትን የሚፃረር ነዉ

https://p.dw.com/p/O0E3
ምርጫምስል DW

የኢትዮጵያ ምርጫ ሒደትና ዉጤት የፍርድ ቤት ብይን ሳያገኝ የሐገሪቱ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የመጨረሻ ያለዉን ዉጤት ትናንት በይፋ ማስታወቁ «ሕገ-ወጥ ነዉ» ሲል የመላዉ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) አስታወቀ።መኢአድ ዛሬ ባወጣዉ መግለጫዉ እንዳለዉ ድርጅቱ የመሠረተዉ ክስ ብይን ሳያገኝ ምርጫ ቦርድ ዉጤት ማወጁ ሕጋዊ ሒደትን የሚፃረር ነዉ።እንደ መኢአድ ሁሉ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክም የምርጫዉን ሒደትና ዉጤት በመቃወም ክስ መስርቷል።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ታደሰ እንግዳዉ ዝር ዝር ዘገባ አለዉ።

ታደሰ እንግዳዉ

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ