የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድና ተቃዋሚዎች
ረቡዕ፣ ጥር 8 2005ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ፣ 33 ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ራሳቸውን ከቀጣዩ አካባቢያዊና የአዲስ አበባ አስተዳደር ምርጫ ስለማግለላቸው የደረሰው ነገር እንደሌለ አስታወቀ ። ፓርቲዎቹ የምርጫ ቦርድ ችግራችንን ሊፈታልን አልቻለም ሲሉ ያቀረቧቸው ጥያቄዎችም አዲስ እንዳልሆኑና በማስረጃም እንዳልተደገፉ ገልጿል ። ማስረጃ በሌለው ጉዳይ ላይ ምንም ማድረግ እንዳልቻለ ያስታወቀው የምርጫ ቦርድ የመወዳደሪያ ምልክት መውሰጃ የጊዜ ገደብ በማለፉ በመጠናቀቁ ፓርቲዎቹ በምርጫው እንደማይሳተፉ የተወቀ ጉዳይ ነው ብሏል ። የፓርቲዎቹ ጊዚያዊ አስተባባሪ ኮሚቴ ከመንግሥትና ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጋር ለመወያየት ፓርቲዎቹ በተደጋጋሚ ያቀረቡት ጥያቄ ዉድቅ ሥለሆነባቸዉ እራሳቸዉን ከምርጫዉ ለማግለል መገደደቸውን ትናንት አስታውቀዋል ። ዝርዝሩን ዮሐንስ ገብረ እግዚዘአብሔር ያቀርብልናል
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ሂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ