1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የሳዑዲ አረቢያ ጉብኝት

ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 22 2007

የመልዕክተኞቹ ቡድን ሳዑዲ አረቢያ ከሚኖሩ ከተመረጡና የተወሰኑ ኢትዮጵያዉን ጋር መነጋገሩም ተሰምቷል። የሳዑዲ አረቢያ ቀጣሪዎች ወይም አሰሪዎች ችግር ያደርሱብናል የሚሉ አብዛኛዎቹን ኢትዮጵያዉያንን ግን አላነጋገረም።

https://p.dw.com/p/1EDhD
ምስል AP

የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አባዱላ ገመዳ የመሩት የመልዕክተኞች ቡድን በሳዑዲ አረቢያ የሚያደርገዉን ጉብኝ ዛሬም እንደቀጠለ ነዉ።ቡድኑ ከሳዑዲ አረቢያ ባለሥልጣናት ጋር የመዋዕለ ነዋይ ፍሰትንና የኮንትራት ሠራተኞችን የሚመለከቱ ዉይይቶችን ማድረጉ ቢዘገብም የወይይቱ ዝርዝር ይዘት ግን በግልፅ አልተነገረም። የመልዕክተኞቹ ቡድን ሳዑዲ አረቢያ ከሚኖሩ ከተመረጡና የተወሰኑ ኢትዮጵያዉን ጋር መነጋገሩም ተሰምቷል። የሳዑዲ አረቢያ ቀጣሪዎች ወይም አሰሪዎች ችግር ያደርሱብናል የሚሉ አብዛኛዎቹን ኢትዮጵያዉያንን ግን አላነጋገረም።በሳዑዲ አረቢያ ተባባሪ ዘጋቢያችንን ነብዩ ሲራክን በስልክ አነጋግሬዋለሁ።

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ