1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የቀድሞው ፕሬዚዳንት የፍርድ ቤት ውሎ

ረቡዕ፣ ጥር 29 2011

አቶ አብዲ መሐመድ በዋና ወንጀል ፈጻሚነት እና አመራር በመስጠት ለ59 ሰዎች ኅልፈት፤ 266 ሰዎች ቀላል እና ከባድ ጉዳት እንዲደርስባቸው፤ ከ412 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ላላቸው ንብረቶች ውድመት ተጠያቂ አድርጓቸዋል አቃቤ ሕግ በክሱ

https://p.dw.com/p/3CrkA
Schild Äthiopisches Bundesgericht
ምስል DW/G.Egziabher

MMT Beri. [A.A - Gerichtsverhandlung- Abdi Mohammed] - MP3-Stereo


የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የቀድሞው ፕሬዚደንት አብዲ መሐመድ የቀረበባቸው ክስ «የተቀነባበረ» መኾኑን ዛሬ ለፍርድ ቤት ተናገሩ።  አቶ አብዲ ይኽን የተናገሩት፦ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራተኛ ወንጀል ችሎት ልደታ ምድብ በቀረቡበት ወቅት ነው። አቶ አብዲ መሐመድ በዋና ወንጀል ፈጻሚነት እና አመራር በመስጠት ለ59 ሰዎች ኅልፈት፤ 266 ሰዎች ቀላል እና ከባድ ጉዳት እንዲደርስባቸው፤ ከ412 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ላላቸው ንብረቶች ውድመት ተጠያቂ አድርጓቸዋል አቃቤ ሕግ በክሱ። አቶ አብዲ ክሱ ገብቷቸው እንደኾን በዳኞች ተጠይቀው፦ «ክሱ በውሸት የተቀነባበረ መኾኑ ገብቶኛል» ማለታቸውን የፍርድ ቤት ውሎውን የተከታተለው የአዲስ አበባው ወኪላችን ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር ዘግቧል። 

ማንተጋፍቶት ስለሺ
ኂሩት መለሰ