1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቲለርሰን ጉብኝት

ማክሰኞ፣ የካቲት 27 2010

ያማሞቶ ትናንት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የኢትዮጵያን ችግር ዉስብስብ ብለዉታል።ከዚሕ ቀደም በአዲስ አበባ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር የነበሩት ያማሞቱ «የተወሳሰበዉን ችግር» ለማቃለል መንግሥታቸዉ የሚረዳበት መንገድ ካለ ርዳታዉን አይቆጥብም

https://p.dw.com/p/2tn2N
Donald Yamamoto (L)
ምስል picture-alliance/dpa/J. L. Scalzo

(Beri.AA) Tellerson`s Visit to Ethiopia-Yamamoto PC - MP3-Stereo

የኢትዮጵያን ፖለቲካዊ ቀዉስ እና ሌሎች ችግሮችን ለማርገብ ዩናይትድ ስቴትስ የምትችለዉን ያክል ልትረዳ እንደምትችል የአሜሪካዉ ተጠባባዊ የአፍሪቃ ጉዳይ ረዳት ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር አስታወቁ።ተጠባባቂ ረዳት ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ዶናልድ ያማሞቶ ትናንት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የኢትዮጵያን ችግር ዉስብስብ ብለዉታል።ከዚሕ ቀደም በአዲስ አበባ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር የነበሩት ያማሞቱ «የተወሳሰበዉን ችግር» ለማቃለል መንግሥታቸዉ የሚረዳበት መንገድ ካለ ርዳታዉን አይቆጥብም።የአሜሪካዉ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ሬክስ ቲለርሰን ምናልባት ነገ ኢትዮጵያን ይጎበኛሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነዉ።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።

ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ