1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ቡና አምራቾችን ተጠቃሚ ያደርጋል የተባለው እቅድ

ረቡዕ፣ መስከረም 5 2014

የኢትዮጵያ ቡና አምራች አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ ያደርጋል የተባለለት ዕቅድን ለማስተግበር ዛሬ  አዲስ አበባ ውስጥ ውይይት አካሄደ። «ቤኔፊት ኮርፖሬሽን ፎር አፍሪካ» የተሰኘውና ምስረታውን አሜሪካ ሜሪላንድ ግዛት ያደረገው የቡናን ግብዓት ለመላክ የሚንቀሳቀሰው ቡድን ዛሬ ውይይቱን አካኺዷል።

https://p.dw.com/p/40Max
Äthiopien Addis Abeba | Africa Forum
ምስል Seyoum Getu/DW

ቡድን አድማሱን ወደ አፍሪቃ ለማስፋትም እየሠራ ነው

የኢትዮጵያ ቡና አምራች አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ ያደርጋል የተባለለት ዕቅድን ለማስተግበር ዛሬ  አዲስ አበባ ውስጥ ውይይት ተካሄደ። «ቤኔፊት ኮርፖሬሽን ፎር አፍሪካ» የተሰኘውና ምስረታውን አሜሪካ ሜሪላንድ ግዛት ያደረገው የቡናን ግብዓት ለመላክ የሚንቀሳቀሰው ቡድን ዛሬ ውይይቱን አካኺዷል። አሜሪካ ኗሪ በኾሆኑ ኢትዮጵያውያን አባላት ቀስቃሽነት የተመሰረተው ይህ ቡድን አድማሱን ወደ አፍሪቃ ለማስፋትም እየሠራ ነው ተብሏል። የኢትዮጵያ የዘርፉ ባለስልጣናትንም ዛሬ ያሳተፈው የውይይት መድረክ የመግባቢያ ሰነድን በመፈራረም ኢትዮጵያ ከዘርፉ የምታገኘውን ተጠቃሚነት እንድታሳድግ ይረዳልም ተብሏል። 
ሥዩም ጌቱ 
ማንተጋፍቶት ስለሺ
እሸቴ በቀለ