የኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ማህበር
ሐሙስ፣ ነሐሴ 19 2008ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ማህበር አገልግሎቶቹን ይበልጥ አንዲያስፋፋ ተጠየቀ ። ዶቼቬለ ያነጋገራቸው የማህበሩ ደንበኞች ማህበሩ እስካሁን ሲሰጥ የቆየውን ጠቃሚ አገልግሎቶቹን በክፍለ ከተሞች እና በክልሎችም አስፋፍቶ እንዲቀጥል ሃሳብ አቅርበዋል ። ከዚህ ሌላ የማህበሩ አገልግሎቶች በተቀላጠፈ መንገድ እንዲሰጡም ደንበኞች ጠይቀዋል ። በቅርቡ የወርቅ ኢዮቤልዮ በዓሉን ያከበረው የኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ማህበር አገልግሎቱን የሚሰጠው ከመንግሥት እና ከግል የጤና ተቋማት በቀጥታ ለሚመጡና በግልም ህክምና ለሚጠይቁ ግለሰቦችም ጭምር ነው ። ዝርዝሩን የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ልኮልናል ።
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ኂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ