1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፓርቲ ፖለቲከኖች አስተያየት

ረቡዕ፣ ነሐሴ 18 2008

የቀድሞዉ የሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ (ሕወሐት) መሥራች አቶ አስገደ ገብረስላሴ እና በቅርቡ ከእስር የተፈቱት የአረና ትግራይ ፓርቲ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል አቶ አብረሐ ደስታ የሐገሪቱን ገዢ ፓርቲ ኢሕአዴግን አምባገነን እና ጨቋኝ ብለዉታል

https://p.dw.com/p/1JoND
ምስል DW/Y. Gebreegziabher

[No title]

የኢትዮጵያን ፖለቲካዊ ቀዉስ ለማስወገድ ብሔራዊ እርቅ እንዲደረግ ሁለት የኢትዮጵያ መንግሥት ተቃዋሚ ፖለቲከኞች ጠየቁ።የቀድሞዉ የሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ (ሕወሐት) መሥራች አቶ አስገደ ገብረስላሴ እና በቅርቡ ከእስር የተፈቱት የአረና ትግራይ ፓርቲ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል አቶ አብረሐ ደስታ የሐገሪቱን ገዢ ፓርቲ ኢሕአዴግን አምባገነን እና ጨቋኝ ብለዉታል።የኢሐዲግን ሥርዓት ለማስወገድ ተቃዋሚ ፓርቲዎች አንድ ወጥ አገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲ እንዲመሰርቱም ፖለቲከኞቹ መክረዋል።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ሁለቱን ፖለቲከኞቹን አነጋግሮ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ