1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ቱሪዝምና የጉብኝት ባህላችን

ሐሙስ፣ መጋቢት 11 2006

የኢትዮጵያ ቱሪዝም ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ የአቶ ሰለሞን ታደሰን አስተያየት ነበር ያደመጥነዉ። በዓለም ላይ ያሉ በርካታ ሃገራት ቱሪዝምን ዋና የኤኮኖሚ ምንጭ በማድረግ በየዓመቱ በሚሊያርድ የሚቆጠር ገንዘብ በማግኘት፤ ቱሪዝምን ጠቃሚ የኤኮኖሚ ዘርፍ ማድረጋቸዉ ይታወቃል። የኢትዮጵያዉያን የጉብኝት ባህል እስከምን ይሆን?

https://p.dw.com/p/1BTIO
Eingang zur ITB 2014
የበርሊን ቱሪዝም ትዕይንት አዳራሽምስል DW/R. Romaniec

ቱሪዝም ከገቢ ማስገኛነቱ ባሻገር ባህልና ሃገርን በማስተዋወቁ ረገድ ከፍተኛ ሚና እንዳለዉ ይታወቃል። ከሳምንታት በፊት የዓለም የቱሪዝም ድርጅቶች ተሳታፊ በሆኑበት በበርሊኑ ዓለማቀፍ የቱሪዝም ድርጅቶች ትዕይንት ላይ ኢትዮጵያ ከሃያ አምስት በላይ የጉዞ ወኪሎችና አስጎብኝ ድርጅቶችን ተሳታፊ ሆነዉ በታል። ኢትዮጵያ በቱሪዝሙ ረገድ ያላት እንቅስቃሴ ምን ይመስላል? በለቱ ዝግጅታችን የምንዳስሰዉ ርዕሳችን ነዉ!
የብሄር ብሄረሰቦች መገኛ የሆነችዉ ኢትዮጵያ፤ከአፍሪቃ ቋርሶችዋን በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባህል ድርጅት « ዩኔስኮ» በማስመዝገብ አንደኛ ደረጃ መያዝዋ ይታወቃል። በቱሪዝም ረገድ ህዝቦችዋን ባህልዋን በማስተዋወቅ እና ጎብኝዎችን በመሳብ ረገድ እያደረገችዉ ያለዉ እንቅስቃሴ ምን ያህል ይሆን፤ በኢትዮጵያ የባህል እና የቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲየታ ወ/ሮ ታደለች ዳለቾ እንደሚሉት፤ የቱሪዝም ልማት ማለት ባህልንም ይጨምራል፤

ከሁለት ሳምንታት በፊት በርሊን ላይ በተካሄደዉ ዓለማቀፍ የቱሪዝም ድርጅቶች ትዕይንት ላይ የኢትዮጵያ የቱሪዝም ድርጅት ቡድንን በመምራት በርሊን ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ቱሪዝም ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ሰለሞን ታደሰ እንደሚሉት ከኢትዮጵያ የመጡት አስጎብኝ ድርጅቶች በበርሊኑ ትዕይንት ላይ ከማንኛዉም ግዜ በተሻለ ጥሩ ግንኙነት ፈጥረናል።

የዓለም ሃገትን በመጎብኘት አዲስ ነገሮችን ለማወቅና ለማየት ጉጉት ካላቸዉ ህዝቦች መካከል ጀርመናዉያን ተጠቃሽ ናቸዉ። በዚህም በየዓመቱ የአለም ሃገራት አስጎብኝ ድርጅቶችን በመጋበዝ በርሊን ላይ ግዙፍ የቱሪዝም ትዕይንት ይደረጋል። በርሊኑ የቱሪዝም ድርጅቶች ትርኢት ላይ ለዘጠኛ ግዜ ተሳታፊ የነበሩት የክብራን አስጎብኝ ድርጅት ዋና ስራ ስኪያጅ አቶ አሰፋ አዘነ እንደሚሉት በርካታ ጀርመናዉያን ኢትዮጵያዉያን ለመጎብኘት እንደሚመጡ እና በርካቶቹ በእድሜ የገፉና ባህላና ታሪክን ለማወቅ የሚፈልጉ ናቸዉ።
በኢትዮጵያ የባህል እና የቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲየታ ወ/ሮ ታደለች በኢትዮጵያ ቱሪዝም እንዲጠናከር ጥረት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ቱሪዝም ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ሰለሞን ታደሰ በበኩላቸዉ ኢትዮጵያዊዉ ራሱ የብሄር ብሄረሰቡን የተለያየ ባህልና አኗኗር ጠንቅቆ ማወቁ ለሃገሪቱ የቱሪዝም ኢንዱስትሪ እድገት ቀዳሚ ስፋራ ሊሰጠዉ የሚገባ ነዉ ባይ ናቸዉ። የክብራን አስጎብኝ ድርጅት ዋና ስራ ስኪያጅ አቶ አሰፋ አዘነ፤ እንደሚሉት የኢትዮጵያን የተለያዩ ክፍሎች የሚጎበኙ ኢትዮጵያዉያኖች አሉ ግን እጅግ በጣም አገር እንወቅ የሚሉ ኢትዮጵያዉያኖች ቁጥር ቅጅግ ጥቂት ነዉ ሲሉ ገልፀዋል። በዚህም የጉብኝት ባህላችን እንዲዳብር ጥረት እየተደረገ መሆኑ ተገልፆአል። የቱሪዝም ኢንዱስትሪን ለማሳደግና የሃገር ባህልን ለማስተዋወቅ ታሪካችን ማንነታችን ማወቅ ይገባናል ያሉንን የዕለቱን እንግዶቻችን እናመሰግናለን ሙሉዉን ቅንብር የድምፅ ማድመጫዉን በመጫን ይከታተሉ !
አዜብ ታደሰ
አርያም ተክሌ

Messe ICC Berlin ITB Messe 2014 in Berlin
ምስል Amine Bendrif
Berlin Sao Tome und Principe
ምስል DW/C. Vieira Teixeira