1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ አንድነት ብሔራዊ ግንባር በዘጠኝ ፓርቲዎች ሊመሰረት ነው

ቅዳሜ፣ ግንቦት 17 2011

ዘጠኝ የፖለቲካ ፓርቲዎች የኢትዮጵያ አንድነት ብሔራዊ ግንባር የተሰኘ ጥምረት ፈጠሩ። የተጣመሩት የፖለቲካ ፓርቲዎች በዛሬው ዕለት ስምምነት ተፈራርመዋል። በቅርቡ ምሥረታውን ያከናውናል የተባለው የዚሁ ግንባር አባላት ሌሎች ተመሳሳይ የፖለቲካ አቋም ያላቸው ፓርቲዎች እንዲቀላቀሏቸው ጥሪ አቅርበዋል።

https://p.dw.com/p/3J4oh
Äthiopien Parteien bilden "Einheitsfront" in Addis Abeba
ምስል DW/Getachew Tedla

በቅርቡ ምሥረታው ይካሔዳል

ዘጠኝ የፖለቲካ ፓርቲዎች የኢትዮጵያ አንድነት ብሔራዊ ግንባር የተሰኘ ጥምረት ፈጠሩ። የተጣመሩት የፖለቲካ ፓርቲዎች በዛሬው ዕለት ስምምነት ተፈራርመዋል። ጥምረቱን የፈጠሩት የኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነት ኮንግረስ፤ የኢትዮጵያ ኅብረ ሕዝብ ብሔራዊ ንቅናቄ፣ የአገው ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ፣ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ሕብረት፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ኮንግረስ፤ የጋምቤላ ሕዝቦች ነፃነት ንቅናቄ፣ የጋምቤላ ሕዝብ ፍትህ ሰላም እና ዴሞክራሲ ንቅናቄ፣ ሸኮ እና አካባቢው ዴሞክራሲያዊ ድርጅት እና የአርጎባ ብሔረሰብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ የተሰኙት ፓርቲዎች ናቸው። በቅርቡ ምሥረታውን ያከናውናል የተባለው የዚሁ ግንባር አባላት ሌሎች ተመሳሳይ የፖለቲካ አቋም ያላቸው ፓርቲዎች እንዲቀላቀሏቸው ጥሪ አቅርበዋል።

ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ 

እሸቴ በቀለ