1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ አየር መንገድ፤ ብራዚልና አፍሪቃ

ረቡዕ፣ ሰኔ 26 2005

ኢትዮጵያናብራዚል ግንኙነታቸዉን እንደሚያስፋፉ እና እንደሚያጠናክሩ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲስ የበረራ መስመር ወደሪዮደጄኒሮ እና ሳኦፖሎ በዘረጋበት ወቅት አሳወቁ።

https://p.dw.com/p/191hC
ምስል Reuters

ብራዚል ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ አፍሪቃ ዉስጥ የምታደርገዉ የኤኮኖሚ እንቅስቃሴ እየተጠናከረ መምጣቱ እየተነገረ ነዉ። በአፍሪቃ ረሃብና ስራ አጥነትን ለመዋጋትም የብራዚልን ተሞክሮ መጋራቷ እንደሚጠቅማት አዲስ አበባ ላይ በዚህ ጉዳይ ላይ ለመከሩ መሪዎች ሃሳብ አካፍለዋል። እንዲያም ሆኖ ብራዚልና አፍሪቃን የሚያገናኝ ቀጥታ የበረራ መስመር ሳይፈጠር ቆይቷል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጀመረዉ በረራም በአጋጣሚዉ በኢትዮጵያና በብራዚል መካከል ያለዉ ግንኙነት እንዲስፋፋ እንደሚረዳ ተገምቷል።  ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ ዘገባ አለዉ

ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ

ሸዋዬ ለገሠ

ሂሩት መለሰ