1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዳዲስ አዉሮፕላኖች

ዓርብ፣ ኅዳር 11 2002

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አሥራ ሁለት A350 የረጅም ርቀት በራሪ አውሮፕላኖችን ለመግዛት ከኤየርባስ ኩባንያ ጋር አንድ ውል መፈራረሙ ባለፈዉ ሳምንት መጨረሻ ላይ ይፋ መሆኑ የሚታወስ ነዉ።

https://p.dw.com/p/Kbwz
A350 የረጅም ርቀት በራሪ አውሮፕላንምስል picture-alliance / dpa/dpaweb

በዛሬው ዕለት ይህንኑ የአዉሮፕላን ግዢ ስምምነት በማስመልከት የኢትዮጽያ አየር መንገድ ባወጣዉ መግለጫ ባለፉት ወራቶች ለግዢዉ ስምምነት የተደረገዉ ድርድር መጠናቀቁ እና አዉሮፕላኖችን ከኤር ባስ ኩባንያ እንደ ኢ.አ በ 2013 አ.ም ለመረከብ የሚያስችለዉን ስምምነት መፈረሙን መገለጹ ወኪላችን ታደሰ እንግዳዉ ዛሪ ከአዲስ አበባ በአደረሰን ዘገባ ጠቁሞናል።

ታደሰ እንግዳዉ/ አዜብ ታደሰ/ ሂሩት መለሰ