1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ኤኮኖሚ

የኢትዮጵያ እና ኬንያ የንግድ ግንኙነት

ዓርብ፣ የካቲት 22 2011

በኢትዮጲያ ሁለት ቀናት የሥራ ጉብኝት ለማድረግ ዛሬ ጠዋት አዲስ አበባ የገቡት ፕሬዝዳንት ኡሁሩ በአሁኑ ሰዓት አዚህ ሀዋሳ በመገኘት የሀዋሳን እንዱስትሪል ፓርክ በመጎብኘት ላይ ይገኛሉ፡፡ አዲስ አበባ ላይ ደግሞ ከመቶ በላይ የኬንያ እና የኢትዮጵያ የንግድ ማኅበረሰብ የተገኙበት የንግድ ጉባኤ እየተካሄደ ነው።

https://p.dw.com/p/3EL9l
Stadtansicht von Addis Abeba Hauptstadt von Aethiopien
ምስል Imago/photothek

መሪዎቹ የሀዋሳን ኢንዱስትሪ ፓርክ ጎብኝተዋል

 ጉባኤው የሁለቱን ሃገራት የንግድ እና የመዋዕለ ንዋይ ፍሰት ትስስር እንደሚያጠናክር ተገምቷል። በተያያዘ ዜናም የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ እና የኬንያው ፕሬዝደንት ዑሁሩ ኬንያታ ዛሬ የሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክን እንደጎበኙ የሀዋሳው ዘጋቢያችን ሸዋንግዛው ወጋየሁ የላከልን ዘገባ ያስረዳል። 

በጉብኝቱ ወቅትም  የሀዋሳ ኢንዱስትሪያል ፓርክ ሥራ አስኪያጅ አቶ ፍፁም ከተማ የፕሬዝዳንቱ ጉብኝት የሁለቱን ሃገራት ምጣኔ ሀብት በንግድና በመዋዕለንዋ ፍሰት ለማስተሳሰር የተጀመረውን ጥረት የማጠናከር ከፍተኛ አስተዋጽዎ እንዳለው ማመልከታቸውን ሸዋንግዛው በላከው ዘገባ አመልክቷል።

ሸዋንግዛው ወጋየሁ
ነጃት ኢብራሒም
ማንተጋፍቶት ስለሺ