የኢትዮጵያ እና የኤርትራ የሰብዓዊ መብት ይዞታ
ዓርብ፣ ግንቦት 5 2003ማስታወቂያ
ድርጅቱ በዓለም ዙሪያ በበርካታ አገራት የሚፈፀሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ባጋለጠበት ዓመታዊ ዘገባው በ 98 አገራትም እስረኞች የሚገረፉና የሚንገላቱ መሆናቸውን እንዲሁም በ 48 አገራት ደግሞ በሰላማዊ መንገድ ተቃውሞ የሚያሰሙ ሰዎች እንደሚታሰሩና እንደሚንገላቱ ይፋ አድርጓል ። አምነስቲ በሰብዓዊ መብት ረገጣ ከከሰሳቸው አገራት ውስጥ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ይገኙበታል ። የለንደኑ ዘጋቢያችን ድልነሳ ጌታነህ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ስለ ሁለቱ አገራት ስላወጣው ዘገባ የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ እና የኤርትራ የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪ ድርጅት ሃላፊዎችን አነጋግሮ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል ።
ድልነሳ ጌታነህ
ተክሌ የኋላ
ሂሩት መለሠ