1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ከየት ወዴት ?

ሰኞ፣ ጥር 27 2005

እግር ኳሱ በመዳከሙ ምክንያትም ህዝቡ ፊቱን ወደ አውሮፓ ሽምፕዮና ጨዋታዎች በማዞር ከሃገሩ ይልቅ የአውሮፓ ክለቦች ጨዋታዎችን መነጋገሪያው ካደረገ ብዙ አመታት አልፈዋል ። ይሁንና በቅርቡ እግር ኳሱ እንሰራርቶ ኢትዮጵያ ከ 31 አመታት በኋላ ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ በአፍሪቃ ዋንጫ ለመሰለፍ በቅታለች ።

https://p.dw.com/p/17wvi

ኢትዮጵያ እስካሁን ዝና ያተረፈችበት የስፖርት ዘርፍ የረዥም ርቀት ሩጫ ነው ኢትዮጵያ ይህ ዝና እያላት ህዝቧ ከሁሉ አብልጦ የሚወደው ግን እግር ኳስ ነው ። እግር ኳስ የህዝቡ ተወዳጅ ጨዋታ ቢሆንም የዛሬ 51 አመት የአፍሪቃ ዋንጫ ባለቤት የነበረችው የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን አቋምና ይዞታ አሽቆልቁሎ ኢትዮጵያ የአፍሪቃም ዋንጫ ማጣሪያን እንኳን ማለፍ ተስኖት ለብዙ አመታት በአህጉራዊም ሆነ አለም አቀፍ ውድድሮች መሰለፍ አለመቻሏ የእግር ኳስ አፍቃሪውንና የስፖርት ቤተሰቦችን ሲያንገበግብ የቆየ ጉዳይ ነበር ። እግር ኳሱ በመዳከሙ ምክንያትም ህዝቡ ፊቱን ወደ አውሮፓ ሽምፕዮና ጨዋታዎች በማዞር ከሃገሩ ይልቅ የአውሮፓ ክለቦች ጨዋታዎችን መነጋገሪያው ካደረገ ብዙ አመታት አልፈዋል ። ይሁንና በቅርቡ እግር ኳሱ እንሰራርቶ ኢትዮጵያ ከ 31 አመታት በኋላ ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ በአፍሪቃ ዋንጫ ለመሰለፍ በቅታለች ። ደቡብ አፍሪቃ ውስጥ በመካሄድ ላይ ባለው በ29 ነኛው የአፍሪቃ ዋንጫ ላይ የተሰለፈው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንም ከተጨወታቸው 3 ግጥሚያዎች በመጀመሪያው አንድ ለአንድ ፣ በሁለቱ ደግሞ 4 ለባዶና ሁለት ለባዶ ተሸንፎ ከመጀመሪያው ዙር ውድድር ወጥቷል ። ኢትዮጵያ ከ 31 አመታት በኋላ በዚህ ውድድር ለመካፈል መቻሏ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ትንሳኤ ወይስ በአጋጣሚ የተገኘ ውጤት ? ያለፈው ጉድለት ምን ነበር የአሁኑስ አያያዝ እንዴት ይታያል ? የዛሬው የውይይት መድረክ ትኩረት ናቸው ። በነዚህ ጉዳዮች ላይ እንዲወያዩልን 4 እንግዶችን ጋብዘናል ። እነርሱም አቶ ተካ አስፋው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ፣ አቶ ፍቅሩ ኪዳኔ የስፖርት ጋዜጠኛ ለረዥም ጊዜ የአለም ኦሎምፒክ ኮሚቴ አባል ሆነው ያገለግሉ ። አቶ ንጉሴ ገብሪ የቀድሞው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋችና አምበልና አቶ በቀለ የእግር ኳስ አፍቃሪ ናቸው ። ውይይቱን ሂሩት መለሰ መርታዋለች

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ