1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሲኖዶስ ጉባኤ

ረቡዕ፣ ግንቦት 14 2011

ጉባኤዉን የመሩት ሁለቱ የቤተክርስቲያኒቱ ርዕሠ-ሊቃነ ጳጳሳት ፓትሪያርኮች አቡነ ማቲያስና አቡነ መርቆሪዮስ ናቸዉ።አቡነ ማቲያስ በጉባኤዉ መፍከፈቻ ለተሰብሳቢዎች እንደነገሩት የምዕመናን ፍልሰትና የመልካም አስተዳደር እጦት የቤተክርስቲያኒቱ ርዕሥ ሆነዉ መቀጠል የለባቸዉም።

https://p.dw.com/p/3IuO2
Äthiopien Addis Ababa - Orthodoxe Kirche hält Generalversammlung
ምስል DW/G. Tedla

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ዛሬ አዲስ አበባ ዉስጥ ተጀምሯል።ጉባኤዉን የመሩት ሁለቱ የቤተክርስቲያኒቱ ርዕሠ-ሊቃነ ጳጳሳት ፓትሪያርኮች አቡነ ማቲያስና አቡነ መርቆሪዮስ ናቸዉ።አቡነ ማቲያስ በጉባኤዉ መፍከፈቻ ለተሰብሳቢዎች እንደነገሩት የምዕመናን ፍልሰትና የመልካም አስተዳደር እጦት የቤተክርስቲያኒቱ ርዕሥ ሆነዉ መቀጠል የለባቸዉም።የኢትዮጵያ መንግሥት ተቃዋሚ ፖለቲከኞች ለግጭትና መለያየት በር ከሚከፍቱ ቅስቀሳዎች እንዲታቀቡም ፓትሪያርኩ አደራ ብለዋል።

ጌታቸዉ ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ 

ነጋሽ መሐመድ

ተስፋአለም ወልደየስ