የኢትዮጵያ ወታደሮች መዉጣትና የሶማሊያ እጣ22 ኅዳር 2001ሰኞ፣ ኅዳር 22 2001ላለፉት 17ዓመታት በግጭትና ጦርነት የታጀበ ህይወት እየገፋ የሚገኘዉ የሶማሊያ ህዝብ ቀጠሮ አልባ ጥቃቶች ቢደርሱም ኑሮዉን ኑሮ ብሎ እየገፋዉ ነዉ።https://p.dw.com/p/G6zhታጣቂዎቹ ጉዞ ወደመቃዲሾምስል APማስታወቂያሰሞኑን የኢትዮጵያ መንግስት ወታደሮቹን ከሶማሊያ ለማዉጣት መወሰኑ በአንዳንድ ሶማሌዎች ዘንድ የጥቃት በትር እንዲቀንስ ያደርጋል የሚል ተስፋን አሳድሯል። እስላማዊ ኃይሎቹ ተጠናክረዉ በሚገኙበት በዚህ ወቅት የተወሰደዉ ርምጃ የሚፈጥረዉን የፀጥታ ክፍተት እያሰቡ የሚሰጉ ወገኖችም አልታጡም።