የኢትዮጵያ ዉሎ

አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
04:06 ደቂቃ
06.10.2016

(Q&A AA) Äthiopien aktuele lage in Äthiopien - MP3-Stereo

በአዲስ አበባ አካባቢ በሚገኙ ከተሞችና ቀበሌዎችም ተቃዉሞዉ ቀጥሎ፤ የመንግስት እና የድርጅቶች መኪኖች መሰባበር ወይም መቃጠላቸዉ ተሰምቷል

 ኢትዮጵያ ዉስጥ በኦሮሚያ መስተዳድር የተጀመረዉ ሕዝባዊ ተቃዉሞ፤ አመፅና ግጭት በአንዳድ አካባቢዎች እንደቀጠለ ነዉ።ባለፉት ሐያ አራት ሰዓታትም ጅማ ዉስጥ ወሕኒ ቤት በእሳት ጋይቶ ቢያንስ አንድ ሰዉ መገደሉ ሲዘገብ፤ ድሬዳዋ ዉስጥ ትናንት ማታ አመፅ ተቀስቅሶ ነበር።በአዲስ አበባ አካባቢ በሚገኙ ከተሞችና ቀበሌዎችም ተቃዉሞዉ ቀጥሎ፤ የመንግስት እና የድርጅቶች መኪኖች መሰባበር ወይም መቃጠላቸዉ ተሰምቷል።የኢትዮጵያ መንግሥት በበኩሉ ለሕዝባዊ ተቃዉሞና አመፅ የኦሮሞ  ነፃ አዉጪ ግንባር (ኦነግ) እና ግብፅን ማዉገዝ ጀምሯል።ነጋሽ መሐመድ የአዲስ አበባ ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔርን በሥልክ አነጋግሮ።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሄር

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ


 

ተከታተሉን