1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

 የኢትዮጵያ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር መግለጫ

ዓርብ፣ ሐምሌ 5 2011

በሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ይሰጥ የነበረዉ ሳምንታዊ ጋዜጣዊ መግለጫ ዛሬ በሚንስትር ደኤታ ኂሩት ዘመናነ እና በአምባሳደር ወይንሸት ታደሰ አማካይነት ነዉ የተሰጠዉ።መግለጫ ሰጪዎቹ ለመቀየራቸዉ የተሰጠ ምክንያት የለም

https://p.dw.com/p/3M09g
Niger Treffen der afrikanischen Union in Niamey
ምስል Getty Images/AFP/I. Sanogo

የአፍሪቃ መሪዎች ጉባኤና የኢትዮጵያ ተሳትፎ

         
የኢትዮጵያ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር ዛሬ በሰጠዉ ሳምንታዊ መግለጫዉ በቅርቡ ኒያሚ-ኒዠር በተደረገዉ የአፍሪቃ ሕብረት ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ «ከፍተኛ» አስተዋፅኦ ማድረጓን አስታወቀ።በሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ይሰጥ የነበረዉ ሳምንታዊ ጋዜጣዊ መግለጫ ዛሬ በሚንስትር ደኤታ ኂሩት ዘመናነ እና በአምባሳደር ወይንሸት ታደሰ አማካይነት ነዉ የተሰጠዉ።መግለጫ ሰጪዎቹ ለመቀየራቸዉ የተሰጠ ምክንያት የለም።መግለጫዉ ግን በኒያሚዉ ጉባኤና ዉሳኔዉ ላይ ያተኮረ ነበር።

ሰለሞን ሙጬ 

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሰ