1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ዐማፂያን ጥምረት

ረቡዕ፣ ጥቅምት 17 2008

የኢትዮጵያ መንግሥትን በጋራ ለመዉጋት ጥምረት ፈጥረናል ያሉ አምስት ዐማፂ ቡድናት የጋራ መርሕ ለመንደፍ ማቀዳቸዉን አስታወቁ። የአምስቱ ቡድናት ከፍተኛ የአመራር ኣባላት ከሦስት ወር ባልበለጠ ጊዜ የጋራ ዓላማና ፕሮግራም እንደሚነድፉም አስታዉቀዋል።

https://p.dw.com/p/1Gv19
12.06.2013 DW Online Karten Basis Äthiopien Englisch

[No title]

አምስቱ ዐማፂ ቡድናት፣ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር፣ የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር፣ የጋምቤላ ህዝቦች ነጻነት ንቅናቄ፣ የሲዳማ ብሔራዊ ነጻነት ግንባርና የቤንሻንጉል ሕዝቦች ነጻነት ንቅናቄ፣ ባለፈዉ ሳምንት ኦስሎ-ኖርዌ ላይ ባደረጉት ስብሰባ «Peoples‘ Alliance for Freedom and Democracy»በምህፃሩ «PAFD»ተብሎ የሚጠራ ጥምረት መመሰረታቸዉን አስታዉቀዋል። አምስቱ ቡድናት የኢትዮጵያ ሕዝብን ይጨቁናል ያሉትን የሐገሪቱን ገዢ ፓርቲ ኢሕአዴግን ከስልጣን ለማስወገድ ከ20 ዓመት በላይ በተናጥል ሲታገሉ መቆየታቸዉን አስታዉቀዋል።

መርጋ ዮናስ

ነጋሽ መሃመድ