1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠርና የአይሁድ አዲስ ዓመት

ሐሙስ፣ መስከረም 6 2008
https://p.dw.com/p/1GYEB



ኢትዮጵያውያን ቤተ- እስራኤሎች በአይሁድ አቆጣጠር መሠረት እሑድ መስከረም 2 ቀን 2008 ዓ.ም ማታ አዲሱን የአይሁድ 5776 ዓመት ጀምረዋል፡፡ «ሮሽ ሃሻናህ» በአማርኛ «ርዕስ ዓመት » ኢትዮጵያውያን ቤተ- እስራኤላዉያንን ጨምሮ አይሁዳዉያን «ሮሽ ሃሻናህ» በመባል የሚታወቀውን አዲስ ዓመታቸዉን ከመስከረም 2 እስከ መስከረም 4 ቀን ማታ ድረስ አክብረዋል፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ ቀጨኔ አካባቢ በሚኘው ቤተ ሰላም ሲናጉግ «ምኩራብ» የቤተ-እስራኤል ማኅበረሰብ በተገኘበት በሃይማኖታዊ ሥርዓት ተከብሯል፡፡ በእለቱ ዝግጅታችን ስለአከባበር ሥነ-ስርዓቱ እንዲሁም ስለ አይሁዳዉያን የዘመን አቆጣጠርና ከኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር ወይም ባሕረ ሃሳብ ጋር ስላለዉ ተዛማጅነት የሚነግሩንን ባለሞያዎች ይዘናል።