1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ የሃይማኖቶች አባቶች ተቃውሞ በግብረ-ሶዶማዊነት ላይ፤

ማክሰኞ፣ ኅዳር 19 2004

በ 16ኛው ዓለም አቀፍ የአባለ-ዘርእ በሽታዎች ጉባዔ ዋዜማ፣ ግብረ ሶዶማውያንየፊታችን ቅዳሜ በአዲስ አበባ፣ ጁፒተር ሆቴል፣ ሊያካሂዱ ያቀዱትን ጉባዔ፣ የሃይማኖት አባቶች በጽኑ ተቃውመውታል።

https://p.dw.com/p/RzCc
ግብረ-ሰዶማዊነት በብዙ አገሮች ፣ ከሃይማኖትና ባህል አኳያ ብርቱ ተቃውሞ እንደገመው ነው--(ምሳሌ፣ቤልግሬድ፣ ሰርቢያ)ምስል picture-alliance/dpa

አስተያየት ሰጪዎችም በበኩላቸው «ድርጊቱ መታሰቡ፤ በራሱ፤ አስጸያፊ ነው» ማለታቸው ተደምጧል።የሃይማኖት አባቶች፣ ይህንን ጉዳይ፣ ጸያፍ፤ ከሥነ-ምግብር ውጭና ባህላችንን የሚያቆሽሽ አጀንዳ ነው በማለት ዛሬ ለዓለም አቀፍና የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኀን ሊሰጡ የነበረው መግለጫ፤ እንዲሁም ለህዝቡ ሊያቀርቡት የነበረው ጥሪ ከጤና ጥበቃ ሚንስትሩ ጋር ከመከሩ በኋላ፣ ለሌላ ጊዜ መተላለፉን ገልጸዋል።

ታደሰ እንግዳው

ተክሌ የኋላ