1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የህግ ማሻሻያ

ሰኞ፣ ሰኔ 25 2010

ጉባኤው መስተካከል ያለባቸው እንዲስተካከሉ፣ አዳዲስ ሃሳቦችም እንዲካተቱ እና መለወጥ የሌለባቸውም እንዲቀጥሉ እንደሚያደርግ የጉባኤው አባል የሆኑት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የህግ መምህር ፕሮፌሰር ጥላሁን ተሾመ  ለዶቼቬለ ተናግረዋል።

https://p.dw.com/p/30gCu
Berhanu Tsegaye
ምስል DW/G. Telda

የህግ ማሻሻያ

በቅርቡ የተቋቋመው የህግ እና ፍትህ ጉዳዮች አማካሪ ጉባኤ የኢትዮጵያን የፍትህ ስርዓት ለማሻሻል የሚያስችሉ ሀሳቦችን ለመንግሥት እንደሚያቀርብ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተናግረዋል። ጉባኤው መስተካከል ያለባቸው እንዲስተካከሉ፣ አዳዲስ ሃሳቦችም እንዲካተቱ እና መለወጥ የሌለባቸውም እንዲቀጥሉ እንደሚያደርግ የጉባኤው አባል የሆኑት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የህግ መምህር ፕሮፌሰር ጥላሁን ተሾመ  ለዶቼቬለ ተናግረዋል። ህጎችን ስራ በማዋል ረገድ የተቋማዊ መዋቅሮች ሚና እና የዳኝነት ነጻነት አማካሪው ጉባኤ ከሚፈትሻቸው ጉዳዮች ውስጥ እንደሚገኙበት ፕሮፌሰር ጥላሁን አስረድተዋል። 


ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ 
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ