1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ የመንጃ ፍቃድ ሕግና ቅሬታዉ

ሐሙስ፣ ሚያዝያ 4 2004

የኢትዮጵያ መንግሥት የደነገገዉ የመንጃ ፍቃድ የትምሕርትና የሥልጠና ደንብ ከባለ ጉዳዮች ድጋፍም ተቃዉሞም ገጥሞታል።አንዳዶች እንደሚሉት የመንጃ ፍቃድ ትምሕርትና ፍቃዱ ከመንግሥት እጅ ወጥቶ በግል ኩባንዮች መያዙ የአሰራሩን ሒደት አቀላጥፎታል

https://p.dw.com/p/14cPv
Autor/Copyright: Yohannes Gebreegziabher, Deutsche Welle Titel: Polizisten in Dire Dawa/Äthiopien Thema: Die Polizei - (nicht immer) Dein Freund und Helfer in Äthiopien Schlagwörter: Äthiopien, Polizei, Sicherheitskräfte Eingestellt 02/2011
ምስል DW

የኢትዮጵያ መንግሥት በቅርቡ የደነገገዉ የመንጃ ፍቃድ የትምሕርና የሥልጠና ደንብ ከባለ ጉዳዮች ድጋፍም ተቃዉሞም ገጥሞታል።አንዳዶች እንደሚሉት የመንጃ ፍቃድ ትምሕርት፥ ሥልጣናና ፍቃዱ ከመንግሥት እጅ ወጥቶ በግል ኩባንዮች መያዙ የአሰራሩን ሒደት አቀላጥፎታል።ሌሎች ግን ሒደቱ የመቀላጠፉን ያክል ለትምሕርቱና ፍቃዱን ለማግኘት የሚከፈለዉ የገንዘብ መጠን የማይነካ ነዉ ባዮች ናቸዉ።እንደገና ሌሎች «ቀልጣፋ» የሚባለዉ መንጃ ፍቃድ የማዉጣቱ ሒደት ሕይወትና ንብረትን ላደጋ ያጋልጣል ባይ ናቸዉ።የድሬዳዋ መንገድ ትራንስፖርት ቅርንጫፍ ሐላፊ አቶ መሐመድ አሕመድ ሥለ ዋጋዉ ዉድነት የሚቀርበዉን ሥሞታ ትክክል ሲሉት፥ ሥለአደጋዉ ግን መጣራት አለበት ይላሉ።ዩሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ዝርዝር ዘገባ አለዉ።

ዮሀንስ ገብረ እግዚያብሄር
ነጋሽ መሐመድ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ