1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ

ሰኞ፣ ነሐሴ 6 2011

የመሥሪያ ቤቱ የሥራ ሃላፊዎች የሃገሪቱ የፖለቲካ ቀውስ፣ ከፍተኛ የኮንትራባንድ ንግድ እና የቀልጣፋ መስተንግዶ አለመዳበር የችግሩ ዋነኛ ምክንያት መሆናቸውን ተናግረዋል።ባለፈው አመት በሶማሌ ክልል ተገኘ የተባለውን በቀላሉ የሚነድ የነዳጅ አይነት መጠን ለመለየት ጥናት እየተደረገ እንደሆነና የምርት ሙከራ ሥራ እየተሰራ መሆኑንም ሃላፊዎቹ ገልጸዋል።

https://p.dw.com/p/3NmdP
Ministerium Minen und Petroleum  Äthiopien Addis Abeba
ምስል DW/S. Muchie

«የኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ የሚያስገኘው የውጭ ምንዛሪ በከፍተኛ መጠን እየቀነሰ ነው» የማእድን ነዳጅና ተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስቴር

የኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ የሚያስገኘው የውጭ ምንዛሪ ከዓመት አመት በከፍተኛ መጠን እየቀነሰ መምጣቱን የማእድን ነዳጅና ተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስቴር አስታወቀ። የመሥሪያ ቤቱ የሥራ ሃላፊዎች ዛሬ በሰጡት መግለጫ ሃገሪቱ የገጠማት የፖለቲካ ቀውስ፣ ከፍተኛ የኮንትራባንድ ንግድ እና የቀልጣፋ መስተንግዶ አለመዳበር የችግሩ ዋነኛ ምክንያት መሆናቸውን ተናግረዋል።ባለፈው አመት በሶማሌ ክልል ተገኘ የተባለው ነዳጅ በቀላሉ የሚነድ የነዳጅ አይነት መጠኑን ለመለየት ጥናት እየተደረገ እንደሆነና የምርት ሙከራ ሥራ እየተሰራ መሆኑንም ሚኒስቴሩ ዛሬ በሰጠው መግለጫ አመልክቷል።በሃገሪቱ ሁለት የወርቅ አምራች ኩባንያዎች ያሉ ሲሆን ከነዚህም ሜድሮክ የተባለው ድርጅት ስራ በማቆሙ እና ኢዛና የተባለውም በገጠመው የውጭ ምንዛሪ እጥረት ለኬሚካል እጥረት ተዳርጎ ለማምረት መቸገሩን ሚኒስቴሩ አሳውቋል። 

Ministerium Minen und Petroleum  Äthiopien Addis Abeba
ምስል DW/S. Muchie

ሰሎሞን ሙጬ

ኂሩት መለሰ 

ነጋሽ መሐመድ