1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ የሠራተኛ እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ማስተባበያ

ሐሙስ፣ ግንቦት 22 2011

የሠራተኛ እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ሄርጎጌ ተስፋዬ ከሳዑዲ መንግሥት በኩል ስለጉዳዩ  ሕጋዊ በሆነ መልኩ  የደረሰን ነገር የለም ብለዋል።ሳውዲ ጋዜት እንደጻፈው ከሆነ ግን ስምምነቱን ከኢትዮጵያ በኩል ተግባራዊ ማድረግ ባለመቻሉ ውሉ ተቋርጧል። ከምክንያቶቹ መካከል ከረመዳን በፊት ኢትዮጵያ ሠራተኖችን አለመላኳ ይገኝበታል እንደ ጋዜጣው።

https://p.dw.com/p/3JVsS
Äthiopien Addis Abeba
ምስል DW/S. Muchie

የሳዑዲ ዐረብያ እና ኢትዮጵያ የሥራ ስምሪት ውል

የውጭ ሃገር የሠራተኛና ሥራ ጉዳዮችን በተመለከት ኢትዮጵያ ከሳዑዲ አረቢያ መንግሥት ጋር የገባችው ስምምነት ገቢራዊ ባለመሆኑ የሳዑዲ ዜጎች ኢትዮጵያዊያን ሠራተኞችን እንዲቀጥሩ ሕጋዊ ሆኖ ተፈቅዶ የነበረው ቪዛ ውድቅ ሆኗል ተብሎ እየወጣ ስላለው መረጃ የሚያውቀው ነገር እንደሌለ የኢትዮጵያ ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። የሠራተኛ እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ሄርጎጌ ተስፋዬ ለዶቼቬለ እንደተናገሩት መሥሪያ ቤታቸው ከሳዑዲ መንግሥት በኩል ስለጉዳዩ  ሕጋዊ በሆነ መልኩ  የደረሰው ነገር የለም። የሳውዲ ተነባቢ ሳውዲ ጋዜት እንደጻፈው ከሆነ ግን ስምምነቱን ከኢትዮጵያ በኩል ተግባራዊ ማድረግ ባለመቻሉ ውሉ ተቋርጧል። ከምክንያቶቹ መካከል ከሙስሊሞች የጾም ወር ረመዳን በፊት ኢትዮጵያ ሠራተኖችን አለመላኳ ይገኝበታል እንደ ጋዜጣው።ወደ ተለያዩ የአረብ ሃገራት ለስራ የሚሄዱ በርካታ ኢትዮጵያዊያን በሃገራቸው እና በሚሄዱበት ሃገር መንግስታት በኩል ህጋዊ የስራ ስምሪት ስምምነት ባለመኖሩ ለሞት ፣ ከፍተኛ የአካል ጉዳት ፣ ለአዕምሮ ህመም ፣ከዚያም ሲያልፍ ለእስር እና ገንዘባቸውን ለመቀማት ሲዳረጉ ቆይተዋል።አብዛኞችም በሚያደርጉት የህገወጥ ጉዞ ለባህርና ለበረሃ ሲሳይ ሆነው ሲቀሩ ፣ በአሸባሪዎች የጥቃት ሰለባ ሲሆኑ ማየት የተለመደ ነው። የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ሰሎሞን ሙጬ ተከታዩን ዘገባ አጠናቅሯል።

ሰሎሞን ሙጬ

ኂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሠ