1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ የተቃውሞ ፓርቲዎችና የከርሞዉ ምርጫ፣

ማክሰኞ፣ ግንቦት 11 2001

በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ፣ ግንቦት 7 ቀን 1997 ዓ ም የተካሄደዉን ምርጫና ያስከተለዉን ሁሉ ያዘከሩበት ስርዓት በተለያዩi አገራት ዋና ዋና ከተሞች ተካሂዷል።

https://p.dw.com/p/HtZV
ምስል AP

ከ 4 ዓመት በፊት የሆነው ሁሉ ሳይረሳ፣ የ 2002 ምርጫ ሊካሄድ 11 ወራት ያህል ነው የቀሩት። ታዲያ አማራጭ የፖለቲካ መርኅ- ግብር ያላቸው የተቃውሞ የፖለቲካ ፓርቲዎች ይሳተፉ? አይሳተፉ? የሚለው አከራካሪ ሐሳብ በብዙዎች ዘንድ የሚብላላ ጥያቄ እንደመሆኑ መጠን፣ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በሰሜናዊው ምዕራብ በምትገኘው ከተማ ፣ በሲያትል በሚኖረው የኢትዮጵያውያን ማኅበረ-ሰብም ከርክር ተደርጎበታል።

አበበ ፈለቀ /ሂሩት መለሰ