1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ የኮምፕዩተር ወንጀል አዋጅ

እሑድ፣ ሰኔ 5 2008

አዋጁ በህገ መንግሥቱ የተደነገጉ የመናገር የመጻፍ መብቶችን ይገድባል፣ ከዚህ ቀደም እንደወጡት እንደ አወዛጋቢዎቹ የፀረ ሽብር እና የበጎ አድራጎትና የእርዳታ ድርጅቶች አዋጆች ዜጎችን ለማፈን ተጨማሪ መሣሪያ ይሆናል ተብሎ እየተተተቸ ነው ። አስፈላጊነቱናና አፈፃጸሙም እያነጋገረ ነው ።

https://p.dw.com/p/1J4gj
Symbolbild Multimedia Auge Cyberwar
ምስል Fotolia/Kobes

የኢትዮጵያ የኮምፕዩተር ወንጀል አዋጅ


የኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በኢትዮጵያ በኮምፒዩተር አማካይነት የሚፈፀሙ ወንጀሎችን የሚመለከት አዋጅ ባላፈው ማክሰኞ አፅድቋል ። አዋጅን ማውጣት ያስፈለገውም በሃገሪቱ የኮምፕዩተር ወንጀልን ለመከላከል ፣ ለመቆጣጠር ለመመርመርና ኤሌክትሮኒክ ማስረጃዎችን ለመሰብሰብ የሚያስችሉ አዳዲስ ሥርዓቶችን በሕግ መደንገግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ እንደሆነ በአዋጁ መግብያ ላይ ሰፍሯል ። ይሁንና አዋጁ በህገ መንግሥቱ የተደነገጉ የመናገር የመጻፍ መብቶችን ይገድባል፣ ከዚህ ቀደም እንደወጡት እንደ አወዛጋቢዎቹ የፀረ ሽብር እና የበጎ አድራጎትና የእርዳታ ድርጅቶች አዋጆች ዜጎችን ለማፈን ተጨማሪ መሣሪያ ይሆናል ተብሎ እየተተተቸ ነው ። አስፈላጊነቱናና አፈፃጸሙም ልዩ ልዩ ጥያቄዎችን አስነስቷል ። አነጋጋሪው የኢትዮጵያ የኮምፕዩተር አዋጅ እና ስጋቶቹ የዛሬው እንወያይ ርዕስ ነው ። ውይይቱን የድምጽ ማዕቀፉን በመጫን ይከታተሉ።

ኂሩት መለሰ

አዜብ ታደሰ