1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ የወደብ ችግር

ማክሰኞ፣ ኅዳር 15 2002

ወደብ አልባ የሆነችው ኢትዮጵያ ለወደብ ኪራይ በየዓመቱ በርካታ ገንዘብ እንደምታወጣ ተገለፀ ። በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪቃ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ዛሬ የቀረበ ጥናት እንዳመለከተው ኢትዮጵያ በጅቡቲ ወደብ ለምታካሂደው የወጪና ገቢ ንግድ በየቀኑ ሁለት ሚሊዮን ዶላር ትከፍላለች ።

https://p.dw.com/p/KeQx
Karte von Äthiopienምስል AP GraphicsBank/DW

በጥናቱ እንደተዘረዘረው ኢትዮጵያ በዓመት ለወደብ ኪራይ የምትከፍለው አገሪቱ ለነዳጅ ዘይት ከምታወጣው ገንዘብ ቀጥሎ ትልቁን ቦታ ይይዛል ። ይህኑ በተመለከተው ስብሰባ ላይ ችግሩን ለማስወገድ ኢትዮጵያ ደረቅ ወደቦችን መገንባትና ያሉትን ማስፋፋት ብቸኛው አማራጯ መሆኑ ተጠቁሟል ። ታደሰ ዕንግዳው ።

ታደሰ ዕንግዳው ፣ ሂሩት መለሰ ፣ ነጋሽ መሀመድ