1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ የዝናም ምንጮች፣

ረቡዕ፣ ነሐሴ 22 2005

የዕለት- ከዕለት ዓለም አቀፍ የአየር ጠባይ መዝጋቢዎች ፤በዓለም ዙሪያ ስለተለያዩ ከተሞችና አካባቢዎች የሙቀት መጠን መግለጽ አይሳናቸውም። ለምሳሌ ያህል፤ የኢትዮጵያ መዲና ፣ አዲስ አበባ ፤ ዛሬ ያለው የሙቀት መጠን ፣ ቢበዛ 19 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ነው።

https://p.dw.com/p/19XXf
ምስል picture alliance/Robert Harding

በአሁኑ ጊዜ በየትኛውም የዓለም ክፍል ስለሚገኝ ከተማም ሆነ አካባቢ የአየር ጠባይ ፤ ሰፋ አድርጎ ማወቅም የሚፈልግ ፤ ስለ አየሩ ንብረት ፤ ስለወቅቶች፣ ስለመሳሰለውና ሌላም- ሌላም መረጃ ማግኘት እምብዛም አይቸገርም።

በአመዛኙ ፣ ወቅቱን የጠበቀ ዝናም ከሚያገኙት ሃገራት አንዷ ኢትዮጵያ መሆኗን ፤ በረጅሙ የዝናም ወቅት ፤ ከሰኔ እስከ ጳጉሜም ሆነ መስከረም፤ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሞንሱን በመባል የታወቀው የተሟላ የዝናም ወቅት ተጠቃሚ መሆኗን፤ ከሰላማዊው ውቅያኖስ በሙቀት መጨመርና መቀነስ «ኤል ኒኞ» ና «ላ ኒኛ» አንዳንዴ በመፈራረቅ ስላላቸው ድርሻ ፤ ዘንድሮ በኢትዮጵያ በዛ ያለ ዝናም የጣለበትን ሁኔታ መነሻ በማድረግ ያነጋገርናቸው ፣ በኢትዮጵያ ብሔራዊው የአየር ጠባይ ጥናት ድርጅት (ኤጀንሲ) የአየር ጠባይ(ሚቲዮሮሎጂ) ትንበያና ማስጠንቀቂያ፤ የሥራ አመራር ዋና ኀላፊ (ዳይሬክተሬት ዳይሬክተር)አቶ ድሪባ ቆሪቻ፤ ባለፈው ሳምንት በሰፊው አብራርተውልን እንደነበረ የሚታወስ ነው። ዛሬም ተጨማሪ ማብራሪያ ያቀርቡልናል።

Nicaragua Rio San Juan
ምስል Yuir Cortez/AFP&Getty Images

ኢትዮጵያ ፣ በዛ ያለ ዝናም እንድታገኝ የህንድና የሰላማዊው ውቅያኖሶች ላቅ ያለ ድርሻ ቢኖራቸውም ፤ አትላንቲክ ውቅያኖስም ሚና አለው ይላሉ አቶ ድሪባ ቆርቻ።

በኢትዮጵያ ብሔራዊ የአየር ጠባይ ጥናት ድርጅት (ኤጀንሲ) የአየር ጠባይ(ሚቲዮሮሎጂ) ትንበያና ማስጠንቀቂያ፤ የሥራ አመራር ዋና ኀላፊ (ዳይሬክተሬት ዳይሬክተር)አቶ ድሪባ ቆሪቻ ስለሰጡን ማብራሪያ እናመሰግናለን።

ተክሌ የኋላ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ